Home የመምህራን ትምህርት አመራር ልማት ዳይሬክቶሬት ተከታታይ ሙያ ማሻሻያን መሰረት ያደረገ ስልጠና ሰጠ::

የመምህራን ትምህርት አመራር ልማት ዳይሬክቶሬት ተከታታይ ሙያ ማሻሻያን መሰረት ያደረገ ስልጠና ሰጠ::

13th December, 2025

የመምህራን ትምህርት አመራር ልማት ዳይሬክቶሬት ተከታታይ ሙያ ማሻሻያን መሰረት ያደረገ ስልጠና ሰጠ::

(ታህሳሳ 3/2018 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የመምህራን ትምህርት አመራር ልማት ዳይሬክቶሬት በተከታታይ ሙያ ማሻሻያ (ተ.ሙ.ማ) እቅድ አስተቃቀድ እና አተገባባበር ላይ ትኩረት ያደረገ ስልጠና ሰጥቷል፡፡

የመምህራን ትምህርት አመራር ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ አበራ በስልጠናው መክፈቻ ባደረጉት ንግግር በስራ ክፍሉ ሲደረጉ በነበሩ ድጋፍና ክትትል ስራዎች ተከታታይ የሙያ ማሻሻያ ላይ ተመሳሳይ አተገባበር እንዲኖር ሰልጣኞች ተከታታይ ሙያ ማሻሻያ እቅድ አዘገጃጀትና አተገባበር ላይ የበለጠ ትኩረት አድርገው እንዲሰሩና ያላቸውን እውቀት ተመሳሳይ በሆነ አተገባበር እንዲፈጽሙ መምህራንን ማብቃትና የረሱትን ነገር ማስታውስ ከሰልጣኞች እንደሚጠበቅ ተናግረዋል፡፡

አቶ ተስፋዬ አያይዘውም ስልጠናውን እየወሰዱ ያሉ የትምህርት አመራሮች አዲስ ጀማሪ መምህራን ቅጥር በሚፈጸም ጊዜ ከነባር መምህራን እኩል ተማሪን የሚያበቁ በውጤትና ስነምግባር የሚያንጹ እንዲሆኑና ከመማር ማስተማር ስራው ጋር በቀላሉ መናበብ እንዲችሉ የተዘጋጁ ሞጁሎች ላይ የቅርብ ክትትልና ድጋፍ እያደረጉ እንዲሰሩ ያግዛል ብለዋል፡፡ አክለውም ሰልጣኞች ከስልጠናው ያገኙትን እውቀት በተግባር ላይ እንዲያውሉ አሳስበዋል፡፡

ስልጠናው የመምህራን ትምህርት አመራር ልማት ዳይሬክቶሬት ባለሙያ በሆኑት በአቶ አበበ ገስጥ አማካኝነት የተሰጠ ሲሆን በስልጠናው የ1ኛ ደረጃ መምህራን ልማት ምክትል ርእሰ መምህራን እና የክፍለ ከተማ መምህራንና ትምህርት አመራር ልማት ቡድን መሪዎች ተሳትፈዋል፡፡


.

Copyright © All rights reserved.