Your valuable insights are crucial in helping us gain a deeper understanding.

Take a survey

እንኳን ወደ አዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ በደህና መጡ!

ትምህርት ለዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ፣ለመልካም አስተዳደር ማስፈን እና ለዘላቂ ልማት መፋጠን ቁልፍ መሳሪያ መሆኑ ይታወቃል፡፡

ትምህርት ይህንን ሚና በተገቢው ሊጫወት የሚችለው ጥራቱ ተጠብቆ ሲሰጥ እና ብቁ ዜጋ ማፍራት ሲቻል ብቻ ነው፡፡ ከዚህ አኳያ በሃገራችን የትምህርተ አቅርቦት ለሁሉም ዜጎች በፍትሃዊነት ለማዳረስ የትምህርትና ስልጠና ፖሊሲ ተነድፎ ወደ ስራ ተገብቷል፡፡ የትምህርትና ስልጠና ፖሊሲውም ድህነትን ለማጥፋትና ሃገሪቱን በልማት ጎዳና ከተራመዱ ሃገሮች ተርታ ለማሰለፍ እንደ ሀገር የተቀመጠውን እራዕይ መሰረት አድርጎ የተዘጋጀ ነው፡፡ ከዚህ አጠቃላይ ማዕቀፍ አንፃር በከተማችን የተከናወኑ መጠነ ሰፊ ስራዎች ባለፉት ዓመታት የከተማችንን የትምህርት ተሳትፎና ፍትሃዊነት በማሳደግ ረገድ አበረታች ውጤቶች የተመዘገቡ ሲሆን የሚሰጠው ትምህርት ጥራቱን የጠበቀ እንዲሆን በማድረግ በሁሉም በጅምር ደረጃ የተሻሉ ውጤቶችን ማየት ተችሏል፡፡

ከተማችን የትምህርት ስራ በተደራሽነቱ እና በፍትሃዊነቱ ረገድ መሰረታዊ ለውጦች የታዩበት ቢሆንም በጥራቱ ረገድ ሰፊ ስራዎች መሰራት እንዳለበት ይታመናል፡፡ ከዚህ መነሻ የአጠቃላይ የትምህርት ጥራት ማረጋገጫ ፓኬጅ ተቀርፆ ወደ ስራ ተገብቷል፡፡ ፓኬጁን መተግበር ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ የትምህርት አመራር የአመራር ብቃትን ለማሳደግ የሚያስችሉ ስልጠናዎች መሰጠታቸው ፣ ለመምህራን ጥራቱን የጠበቀ ትምህርት መስጠት የሚያስችላቸው የቅድመ ስራና የስራ ላይ ስልጠና መሰጠቱ ፣ ስርዓተ ትምህርቱ ከትምህርት ደረጃ የሚጠበቀውን ፕሮፋይል ሊያስጨብጥ የሚችል መሆኑም ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ስራዎች መሰራታቸው ፣ የስነ ዜጋና ስነ ምግባር ትምህርት በስርዓተ ትምህርቱ ተካቶ እንዲሰጥ መደረጉ ፣ የለውጥ መሳሪያዎች ማለትም BPR እና BSC ጥናት መሰረት በማድረግ አዲስ የትምህርት አደረጃጀትና አሰራር እንዲፈጠር በማድረግ ተቋማዊ ለውጥ ለማምጣትና ተሞክሮን ለመለዋወጥ የሚያስችሉ ተግባራት መከናወናቸው እንደዚሁም ይህን ለማጠናከር በክትትልና ድጋፍ ተግባራት እንዲታጀቡ ለማድረግ ጥረት መደረጉ እንደተጠበቀ ሆኖ ከሚጠበቀው አጠቃላይ ውጤት አንፃር ሲታይ የተመዘገበው ውጤት በቂ ነው ማለት አይቻልም፡፡

ስለዚህ ሃገራዊ ህዳሴ እውን የሚያደርግ ትውልድ እየተፈጠረ መሆኑን የሚያሳዩ ተስፋ ሰጪ ለውጦች መታየት በመጀመራቸው ይህንን ደግሞ የማስቀጠል ሃላፊነት የሁሉም የትምህርት ባለድርሻ ማለትም በየደረጃው ያለው የትምህርት አመራር ፣ መምህራን ፣ ተማሪዎች ፣ ወላጆች የግል ባለሃብቶችና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ሃላፊነት ስለሆነ ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ በጋራ እንረባረብ እላለሁ፡፡

ዶክተር ዘላለም ሙላት

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር

ትምህርት ቢሮ ኃላፊ

Upcoming events

27 ተኛዉ ከተማ አቀፍ የትምህርት ጉባኤ

-

09:35 AM - 03:50 PM

ስፖርታዊ ውድድር

-

05:40 PM - 07:40 PM

የተማሪዎች ሩጫ ውድድር

-

10:00 AM - 09:55 PM

Recent news

News
የአራዳ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት የ2017 ዓ.ም የክረምት የተማሪዎችና የመምህራን ስፖርት ንቅናቄ ማስጀመርያ መርሃ ግብር አካሄደ ።

የአራዳ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት የ2017 ዓ.ም የክረምት የተማሪዎችና .. Read More »

News
በትምህርት ሴክተሩ በርካታ ውጤታማ ተግባራት መከናወናቸውን በመስክ ምልከታ ማረጋገጡን ከከተማ አስተዳደሩ የተውጣጣ የሱፐርቪዥን ቡድን አስታወቀ።

የሱፐርቪዥን ቡድን ከቢሮ ጀምሮ እስከ ትምህርት ቤት ድረስ ባካሄደው የድጋፍና.. Read More »

News
በ25/75 ፕሮግራም የተደራጁ ቤት ፈላጊ መምህራንን ወደ ስራ ለማስገባት እንዲቻል የተቋቋመው የቴክኒክ ኮሚቴ እስካሁን ባከናወናቸው ተግባራት ዙሪያ ውይይት ተካሄደ።

በመርሀ ግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ስትራቴጂክ ካውን.. Read More »

Wiki
Knowledge management
Book
Digitial library
Map
Location mapping

Gallery

Notice

notice
የ8ተኛ ክፍል የሚኒስትሪ ውጤት ተለቀቀ

አዲስ አበባ ከተማ የ2017 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል 88.8 % ያህሉ 50% እና ከዛ በላይ በማምጣት ወደ ቀጣዩ የክፍል ደረጃ መሸጋገራቸውን የአዲስ ..

notice
የ2017 የትምህርት ዘመን የትምህርት ጊዜ ሰሌዳ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ2017 የትምህርት ዘመን የትምህርት ጊዜ ሰሌዳ /የትምህርት ካላንደር/

(ሰኔ 7 /2016 ዓ.ም)  በ2017 የትምህርት ዘመን በከተማ አስተዳደሩ ስር ባሉ የ..

notice
ሬሜዲያል ፈተና

በአረፋ በዓል ምክንያት በቀን 9/10/2016 ዓ.ም ሳይሰጥ የዋለው የሬሜዲያል ፈተና ሰኞ (በ10/10/2016 ዓ.ም) በፊዚክስ እና ማክሰኞ (በ11/10/2016 ዓ.ም) በኬሚስትሪ ፈተና እንደሚቀጥል እናሳውቃለን፡፡..

notice
6ኛ ክፍል ፈተና

የ6ኛ ክፍል ፈተና ከሰኔ 12 እስከ 14/2016 ዓ.ም ድረስ ይሰጣል ፡፡

(ሰኔ11/2016 ዓ.ም) የ6ኛ ክፍል ፈተና  ከሰኔ 12 እስከ 14/2016 ዓ.ም ድረስ የሚሰጥ ሲሆን  በከተማ አስተዳደሩ በ183..

FAQ support

We're here to power your growth!

We make sure you have everything you need to succeed as a trainer and edupreneur.

Raise your question

Copyright © All rights reserved.