ትምህርቱ ቢሮው የ90 ቀን የንቅናቄ እቅድ አዘጋጅቶ ወደ ተግባር መግባቱን ተከትሎ በከተማ አስተዳደሩ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች በተዘጋጁ የመማሪያ ጣቢያዎች በመሰጠት ላይ መሆኑን ከልዩ ፍላጎትና የጎልማሶች መሰረተ ትምህርት ዳይሬክቶሬት ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ወንድሙ ኡመር ቢሮው በ2017ዓ.ም የክረምት ወቅት የ90 ቀን የንቅናቄ እቅድ አዘጋጅቶ እያከናወናቸው ከሚገኙ ተግባራት መካከል አንዱ ጎልማሶች በበጎ ፍቃደኛ ወጣቶች የትምህርት አገልግሎት እንዲያገኙ ማስቻል መሆኑን ገልጸው ቢሮው ትምህርቱ በወጣለት መርሀግብር መሰረት በአግባቡ ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑን በጣቢያዎቹ በሚያደርገው ድጋፍና ክትትል ማረጋገጡን በመጥቀስ ትምህርቱን እየሰጡ ለሚገኙ በጎ ፍቃደኛ ወጣቶች ምስጋና አቅርበዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የልዩ ፍላጎትና የጎልማሶች መሰረተ ትምህርት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ገመቺስ ፍቃዱ በበኩላቸው በከተማ አስተዳደሩ 11,000 ጎልማሶችን በክረምት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ ታቅዶ 9,536 ያህሉ በመማር ላይ መሆናቸውን ጠቅሰው ጎልማሶቹ ትምህርቱን ሲያጠናቅቁ የብርሀን ምዘና ወስደው እንደፍላጎታቸው 3ኛ ክፍል ገብተው መደበኛ ትምህርት የሚማሩበት ወይም በቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች ገብተው በሚመርጡት ሙያ የአጭር ጊዜ ስልጠና ወስደው ህይወታቸውን የሚመሩበት አማራጭ መዘጋጀቱን አመላክተዋል።
.