2017 ዓ.ም የተማሪዎች ምዝገባን ኦንላይን ለማከናወን እንዲቻል የቅድመ ዝግጅት ተግባራት እየተከናወኑ እንደሚገኙ ተገለጸ።
(ሰኔ 19/2016 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ልማትና ማስፋት ዳይሬክቶሬት ለክፍለከተማ የቴክኖሎጂና መረጃ ቡድን መሪዎች በ2017 ዓ.ም የተማሪዎች ኦንላይን ምዝገባ ዙሪያ ስልጠና ሰጥቷዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ወንድሙ ኡመር በስልጠናው መክፈቻ ባስተላለፉት መልዕክት ቢሮው በቴክኖሎጂ የተደገፈ የትምህርት አገልግሎት ለመስጠት ከሚያከናውናቸው ተግባራት መካከል አንዱ ተማሪዎችን ኦንላይን በመመዝገብ መረጃቸውን በአግባቡ ማደራጀት መሆኑን ገልጸው ተቋማቱ ወደ ሲስተም ገብተው የ2017 ዓ.ም ተማሪዎችን ኦንላይን የመመዝገቡ ስራ ውጤታማ እንዲሆን የስልጠናው ተሳታፊዎች ከወዲሁ መረጃዎችን በአግባቡ የማጠናከር ስራ መስራት እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ልማትና ማስፋት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ደረጀ ዳኜ በበኩላቸው ስልጠናው ለ2017 ዓ.ም የተማሪዎች ምዝገባ የሚያግዘውን የትምህርት ቤት መረጃ አስተዳደር ሲስተምን (school information management system) በማስተዋወቅ ምዝገባውን ውጤታማ ለማድረግ ታስቦ መዘጋጀቱን ጠቁመው በቀጣይ የመንግስት ትምህርት ቤቶችን ወደ ሲስተም በማስገባት በሚዘጋጀው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ተማሪዎችን ኦን ላይን የመመዝገብ ተግባር እንደሚከናወን አስታውቀዋል፡፡
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
What Sapp: - https://whatsapp.com/channel/0029VaHFiBpA2pLF0lLslK2D
flickr :- https://www.flickr.com/photos/197652854@N04/
You Tube: https://www.youtube.com/@addisababaeducationbureau9728
TikTok፡- https://www.tiktok.com/@aaeducationbureau
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: - http://www.aacaebc.wordpress.com/
Website: - aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com
Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/