በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የጽዳት አስተዳደር ጽ/ቤት በወረዳ 04 ገላን ቁጥር 2 ቅድመ 1ኛ እና 1ኛ ደረጃ ት/ቤት የአንድ ማዕከል የፅዳት ንቅናቄ አካሄደ።
በጽዳት ንቅናቄው የክፍለ ከተማው ጽዳት አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ በየነ ቱሉ ፣ የወረዳ አመራሮች ፣ የከተማና የክፍለ ከተማ ሰራተኞች ፣ መምህራን ፣ የፀጥታ አካላት እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።
የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ጽዳት አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ በየነ ቱሉ ቆሻሻ ከራስ የሚመነጭና በአግባቡ ከተወገደ ሀብት ማድረግ የሚቻል መሆኑን በማንሳት የነገ ሀገር ተረካቢ ተማሪዎች ትምህርት ቤታቸውን ፅዱ በማድረግ ቆሻሻን በአግባቡ በማስወገድ ኃላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ተናግረዋል።
የወረዳ 04 ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ቤዛዊት ተዘራ በበኩላቸው ተማሪዎች ንፅህናን ከራሳቸው በመጀመር ቆሻሻን በአግባቡ በማስወገድ ፅዱ ውብ አካባቢን በመፍጠር እንዲሁም ፅዳትን ባህል በማድረግ የሀገሪቱን ብልፅግና ማረጋገጥ እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል።
በፅዳት ንቅናቄው ተማሪዎች አስተማሪ ጭወውት ፣ ግጥም ፣ ውዝዋዜ ያቀረቡ ሲሆን በተጨማሪም ጥያቄና መልስ አካሂደዋል።
.