Announcement በትምህርት ቤቶች ውስጥ የተቋቋሙ የመንገድ ደህንነት ክበባት አባል የሆኑ ረዳት የተማሪ ትራፊክ ፖሊሶች ተማሪዎች መንገድ ላይ ላጋጥማቸው ከሚችሉ አደጋዎች እንዲጠብቁ በመስራት ላይ መሆናቸዉን ገለጹ፡፡

በትምህርት ቤቶች ውስጥ የተቋቋሙ የመንገድ ደህንነት ክበባት አባል የሆኑ ረዳት የተማሪ ትራፊክ ፖሊሶች ተማሪዎች መንገድ ላይ ላጋጥማቸው ከሚችሉ አደጋዎች እንዲጠብቁ በመስራት ላይ መሆናቸዉን ገለጹ፡፡

21st March, 2026

በትምህርት ቤቶች ውስጥ የተቋቋሙ የመንገድ ደህንነት ክበባት ተማሪዎች መንገድ ላይ ላጋጥማቸው ከሚችሉ አደጋዎች እንዲጠብቁ በመስራት ላይ መሆናቸዉን የዝግጅት ክፍላችን ያነጋገራቸው የክበባቱ አባላት የሆኑ ረዳት የተማሪ ትራፊክ ፖሊሶች ተማሪዎች ገልጸዋል፡፡

 ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት ሲመጡና ከትምህርት ቤት ወደቤታቸው ሲመለሱ በመንገድ ላይ ሊገጥማቸው ከሚችሉ አደጋዎች እራሳቸዉን እንዲጠብቁ ለማድረግ በትምህርት መግቢያና መውጫ ሰዓታት ላይ በትምህርት ቤቶች አካባቢ ተማሪዎችን ከማስተናበር ባለፈ በትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ የሰልፍ ስነስርዓት በስርዓቱ እንዲካሄና የመንገድ ደህንነት ግንዛቤዎችን ለተማሪዎች በመስጠት ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

ተማሪዎች መንገድ ሲያቋርጡ ሊከተሏቸው ከሚገቡ ዋና ዋና የደህንነት ደንቦች መካከል ሁልጊዜም በዘብራ (የእግር መሻገሪያ) ወይም በትራፊክ መብራት ባሉባቸው ቦታዎች ብቻ መሻገር ፣ መንገድ ከመሻገር በፊት በመንገዱ ዳር ቆሞ ወደ ግራ፣ ወደ ቀኝ፣ ከዚያም ደግሞ ወደ ግራ በማየት መኪና አለመኖሩን ማረጋገጥ ፣ መኪናዎች ሙሉ በሙሉ መቆማቸውን ሳይረግጡ ወደ አስፋልቱ አለመግባት ፣ ከአሽከርካሪዎች ጋር ዓይን ለዓይን በመገጣጠም (eye contact) እንዳዩዋቸው ማረጋገጥ ፣ መንገድ ሲያቋርጡ በእርጋታና በፍጥነት መሻገር እንጂ መሮጥ ወይም መጫወት እንደሌለባቸው ፣ ስልክ ከመጠቀም፣ የጆሮ ማዳመጫ (earphones) ከማድረግና ከመሳሰሉት ትኩረት የሚከፋፍሉ ነገሮች መቆጠብ እንደሚያስፈልግ ፣ ሁልጊዜም ለእግረኛ በተከለለ መንገድ ላይ መጓዝ እንደሚገባ የእግረኛ መንገድ ከሌለ ደግሞ የሚመጡ መኪናዎችን ፊት ለፊት እያዩ (በስተግራ በኩል) መጓዝ እንደሚመከር ፣ ቆመው ካሉ ትላልቅ መኪናዎች ጀርባ ወይም መሃል ድንገት ወጥቶ መሻገር ለአሽከርካሪዎች ስለማይታዩ በጣም አደገኛ መሆኑ ተጠቃሾች መሆናቸዉን ገልጸዋል፡፡

ተማሪዎቹ አሽከርካሪዎች የራሳቸዉንና  የወገኖቻቸዉን  ህይወት እና አካል የመጠበቅ ድርብ ሀላፊነት ሰላለባቸው በጥንቃቄ እና በማተዋ እንዲያሽከረክሩ ጠይቀዋል፡፡

.

Copyright © All rights reserved.