Announcement በየትንቢተ ኤርሚያስ ቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ከመደበኛ ትምህርታቸው ጎን ለጎን የእደ ጥበብ ሙያ ስልጠና እየተሰጣቸው መሆኑ ተገለጸ።

በየትንቢተ ኤርሚያስ ቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ከመደበኛ ትምህርታቸው ጎን ለጎን የእደ ጥበብ ሙያ ስልጠና እየተሰጣቸው መሆኑ ተገለጸ።

21st March, 2026

በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 አስተዳደር ስር የሚገኘው ትምህርት ቤቱ ተማሪዎች በትምህርት ብቻ ሳይገደቡ በተግባር የሚማሩ ክህሎቶችን እንዲያገኙ የተለያዩ የእደ ጥበብ ስራዎች ላይ ስልጠና በመስጠት ላይ ይገኛል።

በዚህም ተማሪዎች የስራ ባህልን እንዲያጎለብቱ ፣ የፈጠራ ችሎታቸውን ለማጠናከር እና ወደፊት የሚያገለግላቸውን ተግባራዊ ክህሎት ለማግኘት እድል እያገኙ ያግዛቸዋል።

የእደ ጥበብ ስልጠናው ከትምህርት ጥራት ማሻሻል ጋር ተያይዞ ተማሪዎች እውቀታቸውን በተግባር እንዲያጠናክሩ የሚያግዝ መሆኑ ከክፍለ ከተማው ያገኘነው መረጃ የሚያሳይ ሲሆን ይህም ተማሪዎች በመማር ሂደታቸው ውስጥ ተሳትፎአቸውን እንዲጨምሩ እና የራሳቸውን ፈጠራ አቅም እንዲያሳድጉ እንደሚያግዝ ተመላክቷል።

በተጨማሪም ይህ አሰራር ተማሪዎች ከህፃናትነታቸው ጀምሮ የስራ ክብርን እንዲገነዘቡ እና በፈጠራ ስራዎች ላይ እንዲሳተፉ የሚያበረታታ መሆኑ ተጠቁሟል።

ትምህርት ቤቶች ውስጥ የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል እና ተማሪዎችን በተግባር የተደገፈ እውቀት እንዲያገኙ የሚያግዙ መርሀ ግብሮች በተከታታይ እየተተገበሩ የሚገኙ ሲሆን መሰል ተግባራት በፈጠራ እና በሙያ ክህሎት የተዘጋጁ ዜጎች እንዲፈሩ የሚያግዝ ነው።

.

Copyright © All rights reserved.