Home የመምህራንን የማህበር የቤት ግንባታ ለማከናውን የተደራጁ ማህበራትና ኮንትራክተሮችን በማገናኘት በቅንጅት ለመስራት የሚያስችል የጋራ ስራ አቅጣጫ ተቀመጠ።

የመምህራንን የማህበር የቤት ግንባታ ለማከናውን የተደራጁ ማህበራትና ኮንትራክተሮችን በማገናኘት በቅንጅት ለመስራት የሚያስችል የጋራ ስራ አቅጣጫ ተቀመጠ።

07th February, 2026

የመምህራንን የቤት ግንባታ ለማከናውን የተደራጁ ማህበራትና ኮንትራክተሮችን በማገናኘት በቅንጅት ለመስራት የሚያስችል የጋራ ስራ አቅጣጫ የተቀመጠ ሲሆን በመድረኩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ክቡር ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር እንጂነር ቶማስ ደበሌ ፣ የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ተመስገን ወንድሙ ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መምህራን ማህበር ፕሬዝዳንት አቶ ድንቃለም ቶሎሳ ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ አሊ ከማል ፣ የተደራጁ ማህበራት ፣ ኮንትራክተሮች እና ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት ተገኝተዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ክቡር ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ለዚህ ታሪካዊ ቀን እንኴን አደረሳችሁ! እንኳን ደስ አላችሁ በማለት በዛሬው እለት በክብርት ከንቲባ አዳነች አቤቤ የተጀመረው የመምህራን የጋራ ቤት ግንባታ ያለምንም መስተጋጎል በተቀመጠለት ጊዜ ሰሌዳ መሰረት እንዲጠናቀቅ የተደራጁ ማህበራት ከኮንትራክተሮች ጋር በጋራ በመናበብና በቅንጅት ሊሰሩ ይገባል ብለዋል፡፡

ሀላፊው አክለዉም ኮንትራክተሮች ቤቱን ገንብቶ ለማጠናቀቅ ቃል በገቡት መሰረት በቅንጅት በመስራትና ስራዉን በማጠናቀቅ ለመምህራን እንዳስረክቡ አደራ የተጣለባቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር እንጂነር ቶማስ ደበሌ በበኩላቸው ሀገር በተማረ የሰው ሀይል ይቀየራል ያሉ ሲሆን ይህንን የተማረ የሰው ሀይል ለሚያፈሩ መምህራን የሚሰረው የመምህራን የማህበር ቤት በተያዘለት ጊዜ ገደብ እንዲጠናቀቅ ኮንትራክተሮች ከተደራጁ ማህበራት ጋር በመስራት ለስራው ውጤታማነት የበኩላቸውን ሚና ሊወጡ ይገባል ብለዋል፡፡

የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ተመስገን ወንድሙ በበኩላቸው ኮንትራክተሮች የሚገነቡት ቤት ላስተማራቸው መምህራን በመሆኑ እጅግ ኩራት ሊሰማቸው እንደሚገባ ጠቁመው የማማከሩን አገልግሎት ዩኒቨርሲቲው በውጤታማነት የሚያከናዉን መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መምህራን ማህበር ፕሬዝዳንት አቶ ድንቃለም ቶሎሳ በበኩላቸው የመምህራን የጋራ ቤት ግንባታ እዚህ ምዕራፍ ላይ እንዲደረስ ከፍተኛ አስተዋጽዎ ላደረጉት አካላት በሙሉ ምስጋና አቅርበዋል፡፡


.

Copyright © All rights reserved.