Announcement የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ልማትና ማስፋፋት ዳይሬክቶሬት በኢትዮ ኮደርስ ዙሪያ ለክፍለ ከተማ ትምህርት ፅ/ቤት ባለሙያዎች ስልጠና ሰጠ፡፡

የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ልማትና ማስፋፋት ዳይሬክቶሬት በኢትዮ ኮደርስ ዙሪያ ለክፍለ ከተማ ትምህርት ፅ/ቤት ባለሙያዎች ስልጠና ሰጠ፡፡

15th November, 2025

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ልማትና ማስፋፋት ዳይሬክቶሬት በኢትዮ ኮደርስ ዙሪያ በሁሉም ክፍለ ከተማ ትምህርት ፅ/ቤት የሚገኙ አስተባባሪዎችና ቡድን መሪዎች ስልጠና ሰጥቷል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊና የዘርፍ አስተባባሪ አቶ ሳምሶን መለሰ ኢትዮ ኮደርስን በተመለከተ ለትምህርት ማህበረሰቡ በከተማ ደረጃ ትልቅ ንቅናቄ በማድረግ በመዋቅሩ ውስጥ ያሉ ሁሉ ስልጠናውን እንዲወስዱ መደረጉን ገልጸው በዚህ ሂደት ያለፉና ሰርተፍኬት የወሰዱ አካላት ሲስተም ላይ upload እንዲያደርጉ በተሰጠው አቅጣጫ መሰረት ስልጠናው upload የማድረግ እውቀትን እንደሚያስጨብጥ ተናግረዋል፡፡ ሰልጣኞችም ከስልጠናው በሚያገኙት እውቀት በመውሰድ የጽ/ቤቱን ባለሙያዎች በመደገፍ ያገኙትን እውቀት በተገቢ ሁኔታ እንዲያስተላልፉ አቅም ይፈጥራል ብለዋል::

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ዲናኦል ጫላ በበኩላቸው በትምህርት ተቋማት ካለው የሰው ኃይል አንጻር ሲስተሙ የሚጠበቀውን ያህል ሰው እንዳልሰለጠነ ያሳያል ብለው የተሰጠንን ኮታ ለማዳረስ እንደ ክፍለከተማ ትኩረት ተሰጥቶ እንዲሰራበት አቅጣጫ ሰጥተዋል፡፡

ስልጠናውን የወሰዱና ሰርተፍኬት ያገኙ አካላት ወደ ሲስተም upload ለማድረግ እንዲሁም ስልጠናውን ያልወሰዱ አካላት በምን መልኩ ስልጠናውን መጀመርና ማጠናቀቅ እንዳለባቸው ግንዛቤ የሚሰጥ ስልጠና የአይሲቲ ባለሙያ በሆኑት አቶ እንዳሻው አማካኝነት ተሰጥቷል፡፡

.

Copyright © All rights reserved.