Announcement ተማሪዎች ያላቸውን የተፈጥሮ የፈጠራ ክህሎት በተግባር እንዲያሳዩ የሳይንስና የፈጠራ ስራ አውደ ርእዮች ሚናቸው የጎላ መሆኑ ተገለጸ፡፡

ተማሪዎች ያላቸውን የተፈጥሮ የፈጠራ ክህሎት በተግባር እንዲያሳዩ የሳይንስና የፈጠራ ስራ አውደ ርእዮች ሚናቸው የጎላ መሆኑ ተገለጸ፡፡

28th March, 2026

ተማሪዎች ያላቸውን የተፈጥሮ የፈጠራ ክህሎት በተግባር እንዲያሳዩ የሳይንስና የፈጠራ ስራ አውደ ርእዮች ሚናቸው የጎላ መሆኑ ተገለጸ፡፡  

(መጋቢት 17/2018 ዓ.ም) “በሳይንስና ፈጠራ ስራ የተካነ ትውልድ ለተምሳሌታዊ ሀገር!” በሚል መሪ ሀሳብ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ በወረዳ 02 የሳይንሰና የፈጠራ ስራ አውደ ርዕይ ተካሄደ፡፡

መድረኩ በከተማ ደረጃ በ2018 የትምህርት ዘመን የሚካሄደው 11ኛው ከተማ አቀፍ የሳይንስና ፈጠራ ስራ አውደ ርዕይ አካል ሲሆን በውድድሩ ላይ በወረዳው የሚገኙ የመንግስትና የግል ትምህርት ቤት ተማሪዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

ይህ መርሃ ግብር ተማሪዎች ያላቸውን የተፈጥሮ የፈጠራ ክህሎት በተግባር እንዲያሳዩ ከማስቻሉም ባለፈ ለሳይንስ ትምህርቶች ያላቸውን ዝንባሌ ለማሳደግ ትልቅ አቅም ያለው ነው። 

ታዳጊዎች ገና በለጋ እድሜያቸው ከፈጠራ ስራዎች ጋር መተዋወቃቸው ለወደፊት የትምህርት ዘመናቸው መሰረት ከመሆኑም በላይ ዛሬ የታዩት ጅማሮዎች ነገ ለሀገር ተስፋ የሚሆኑ ታላላቅ የቴክኖሎጂ ውጤቶች መገኛ እንደሚሆኑ ተመላክቷል።

ከዚህም በተጨማሪ መሰል ውድድሮች የተማሪዎችን የምርምር መንፈስ በማነቃቃትና በራስ የመተማመን አቅማቸውን በመገንባት ረገድ ያላቸው ሚና የላቀ ነው፡፡

ብቁና የፈጠራ ተሰጥኦ ያለው ትውልድ ለማፍራት እንዲቻልም፣ ታዳጊዎችን በሳይንስና ቴክኖሎጂ የማብቃት ጥረት በየደረጃው ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ በአውደ ርዕዩ ላይ ተገልጿል።


.

Copyright © All rights reserved.