Announcement በተማሪዎችና መምህራን የሚሰሩ የፈጠራ ስራዎች ወደ ተግባር ተቀይረው ለሚፈለገው አላማ እንዲውሉ ትኩረት አድርጎ በመስራት ላይ መሆኑን የጉለሌ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

በተማሪዎችና መምህራን የሚሰሩ የፈጠራ ስራዎች ወደ ተግባር ተቀይረው ለሚፈለገው አላማ እንዲውሉ ትኩረት አድርጎ በመስራት ላይ መሆኑን የጉለሌ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

18th April, 2026

ጽህፈት ቤቱ "በሳይንስና ፈጠራ የተካነ ትውልድ ለተምሳሌታዊ ሀገር" በሚል መሪ ቃል የ2018 ዓ.ም የሳይንስና የፈጠራ ስራ አውደ ርዕይ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት አካሄደ።
የጉለሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ወልዴ ወገሴ በመርሀግብሩ ባስተላለፉት መልዕክት ትምህርት ለአንድ ሀገር ሁለንተናዊ እድገት መሰረት ከመሆኑ ባሻገር ለማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን ጠቁመው በክፍለ ከተማው የሚገኙ የትምህርት ተቋማት ችግር ፈቺ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ስራዎችን መፍጠር የሚችሉ ተማሪዎችንና መምህራንን ማፍራት እንዲችሉ የክፍለ ከተማው አስተዳደር የሚጠበቅበትን ድጋፍ በማድረግ ላይ መሆኑን በመግለጽ በአውደ ርዕዩ የቀረቡ የፈጠራ ስራዎች ወደ ተግባር ተቀይረው ለሚፈለገው አላማ እንዲውሉ በትኩረት መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የቢሮ ኃላፊ አማካሪ ወይዘሮ አበበች ነጋሽ በበኩላቸው ከተማ አስተዳደሩ በፈጠራ የተካነ ትውልድ ለሀገር ብልጽግና የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን በመገንዘብ ለሳይንስና የፈጠራ ስራ ትኩረት አድርጎ በመስራት ላይ መሆኑን አስታውሰው አውደ ርዕዩ ተማሪዎች በክፍል ውስጥ በንድፈ ሀሳብ የተማሩትን ትምህርት በተግባር ቀይረው ስራዎቻቸውን ለተመልካች የሚያሳዩበትን እድል የሚያመቻች በመሆኑ ቢሮው ለዘርፉ የሚሰጠውን ትኩረት አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን አመላክተዋል።

አውደ ርዕዩ በትምህርት ቤትና ወረዳ ደረጃ ተካሂዶ አሸናፊ የሆኑ ስራዎች ተማሪዎችና መምህራን የፈጠራ ስራዎቻቸውን በክፍለ ከተማ ደረጃ ለተመልካች ማቅረባቸውን የጉለሌ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ባርኬ በቴ ገልጸው የፈጠራ ስራዎቹ ወደ ተግባር ተቀይረው ለሚፈለገው አላማ እንዲውሉ ጽህፈት ቤቱ ከባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ የሚሰራ መሆኑን አስታውቀዋል።

.

Copyright © All rights reserved.