የልደታ ክ/ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት የክ/ከተማው የወ.ተ.መ.ህ ስራ አስፈፃሚ በ2017 ዓ.ም የወተመህ የስራ አፈጻጸም ሪፖርትና በ2018 ዓ.ም የ1ኛ ሩብ ዓመት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ውይይት አካሂዳል፡፡
በውይይት መድረኩ ላይ የክፍለ ከተማው ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍራኖል ሞሲሳ ፣ በሃገር ደረጃ የወተመህ ፕሬዚዳንት እና የልደታ ክ/ከተማ የወተመህ ስራ አስፈጻሚ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ሃሰን ሽፋ እና የትምህርት ጽ/ቤት አስተባባሪ አቶ አቡበከር አህመድ እንዲሁም የክ/ከተማ እና የወረዳ የወ.ተ.መ.ህ ስራ አስፈጻሚ አባላት ተሳታፊ ሆነዋል።
በውይይቱ ላይ በክፍለ ከተማው በ2017 ዓ.ም በወተመህ አደረጃጀት የተሰሩ ስራዎች ፣ የነበሩ ጥንካሬዎች፣ የነበሩ ክፍተቶችን እንዲሁም የቀጣይ የትኩረት ነጥቦችን እና በ1ኛ ሩብ ዓመት የተሰሩ ስራዎችን የወተመህ ስራ አስፈጻሚ አቶ ሃሰን ሽፋ አቅርበው ውይይት ተደርጓል።
.