About በትምህርት ለትዉልድ ንቅናቄ ሁለት ሚሊየን ሁለት መቶ አምስት ሺህ ብር የሚያወጣ በድጋፍ የተገኘ የስፖርት ትጥቅ ለትምህርት ቤቶች ተሰራጨ።

በትምህርት ለትዉልድ ንቅናቄ ሁለት ሚሊየን ሁለት መቶ አምስት ሺህ ብር የሚያወጣ በድጋፍ የተገኘ የስፖርት ትጥቅ ለትምህርት ቤቶች ተሰራጨ።

12th July, 2025

የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳዳር ትምህርት  ጽ/ቤት በአስተዳደሩ ስር ለሚገኙ ትምህርት ቤቶች በድጋፍ የተገኙ  የስፖርት ትጥቆችን አበርክቷል።

የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ከበደ ዲራባ እንደገለፁት በዛሬው ዕለት ከ2,205,000 ብር የሚያወጣ በድጋፍ የተገኘ የስፖርት ትጥቅ ትምህርት ቤቶች ከመማር ማስተማር ባሻገር በአዕምሮ የጎለበተ በአካል የዳበረ ትውልድ ለማፍራት ስፖርታዊ ውድድሮችን እንዲጠናክሩ ለማስቻል ያለመ መሆኑን ተናግረዋል ።

በተጨማሪም ታዳጊዎች በስነ ምግባር እንዲታነፁ ፣ አልባሌ ቦታ እንዳይውሉ ፣ ወንድማማችነት፣ አብሮነትና አንድነትን ለማዳበር አይተኬ ሚና እንዳለው የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ኮሙኒኬሽን ዘግባል።

.

Copyright © All rights reserved.