የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚከበረውን አካል ጉዳተኞች ቀን በማስመልከት አካል ጉዳተኛ ለሆኑ ተማሪዎች እና የድጋፍ መስጫ ማዕከላት የግብዓት ድጋፍ አደረገ::
የግብአት ድጋፉን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ በመገኘት ያስረከቡ ሲሆን የልዩ ፍላጎት ላላቸው ተማሪዎች የሚሆኑ ዊልቼር ፤ ክራንች ፤ ኬን ፤ ማዳመጫ መሳሪያ እና ለድጋፍ መስጫ ማእከላት መማር ማስተማር ድጋፍ የሚሆኑ የተለያዩ ግብአቶች ድጋፍ አድርገዋል፡፡
ሀላፊው ድጋፉን ባደረጉበት ወቅት የአካል ጉዳት ያላቸው ተማሪዎች ከሌሎቹ እኩል በትምህርት ስርዓቱ ውስጥ እንዲያልፉና ውጤታማ እንዲሆኑ ቢሮው ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሠሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ቢሮ ሃላፊው አክለውም በዘንድሮው የትምህርት ዘመን በትምህርት ላይ ያሉ ልዩ ፍላጎት ያላቸው ተማሪዎች ከ34 ሺ በላይ መሆናቸውን ተናግረው በቀጣይነት ተማሪዎቹን ውጤታማ ለማድረግ ቢሮው ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በርብርብ እንደሚሰራ አብራርተዋል፡፡
.