በትምህርት ቤቶች ውስጥ የሚገኙ ላብራቶሪዎች የዘመኑና ወቅቱን የዋጁ እንዲሆኑ በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ፡፡
(የካቲት 5/2018 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በትምህርት ቤቶች ውስጥ በሚገኙ ላብራቶሪዎች ውስጥ ለመማር ማስተማር ስራዉ አገልግሎት ሲሰጡ የቆዩና ጊዜያቸው አልፎ ያልተወገዱ ኬሚካሎችን ለማስወገድ ብሎም በቀጣይ በዘመናዊነት ለማደራጀት በሚያስችል ጥናት ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ክቡር ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ፣ የቢሮ ስትራቴጂክ ካውንስል አባላት ፣ የስርዓተ ትምህርት ዳይሬክተሮችና በለሙያዎች እንዲሁም የኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ ምሁራን በተገኙነት ውይይት አካሄዳል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ክቡር ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ በትምህርት ቤቶች በሚገኙ ላብራቶሪዎች ውስጥ ለመማር ማስተማር ስራዉ አገልግሎት ሲሰጡ የቆዩና በአንዳንድ ትምህርት ቤቶች ያልተወገዱ ኬሚካሎች መኖራቸዉን ጠቁመው ጊዜያቸው ያለፉ ኬሚካሎችን ለማስወገድ እንዲቻል በጥናት ላይ መሰረት ያደረገ ስራ ለማከናወን ጥናቱ በኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ አማካኝነት መከናወኑን ጠቅሰዋል፡፡
ሀላፊው አክለዉም በትምህርት ቤቶች ላብራቶሪ ውስጥ የሚገኙ ኬሚካሎች ቆጠራ በጥናቱ ውስጥ መካተቱን አመላክተው በቀጣይ ጥናቱ ላይ መሰረት ያደረገ በትምህርት ቤቶች የዘመነና ወቅቱን የዋጀ ላብራቶሪ እንዲኖር የተጀመሩ ስራዎችን በማጠናከር የሚሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ጥናቱ በኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ መምህር በሆኑት በዶ/ር ዩፍሩ ዋቅቶሌ አማካኝነት ቀርቦ ውይይት ተካሄዳል፡፡

.