Announcement የትምህርት ቤት ምገባ ስርዓት መጠነ ማርፈድን ፣ መቅረትንና መድገምን በመቅረፍ የተማሪዎች ውጤት እንዲሻሸል ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ መሆኑ ተገለጸ፡፡

የትምህርት ቤት ምገባ ስርዓት መጠነ ማርፈድን ፣ መቅረትንና መድገምን በመቅረፍ የተማሪዎች ውጤት እንዲሻሸል ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ መሆኑ ተገለጸ፡፡

21st March, 2026

የዝግጅት ክፍላችን በጉለሌ ክፍለ ከተማ በሚገኘው ድል በትግል ቅድመ አንደኛ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመገኘት ያነጋገራቸዉ የትምህርት ቤቱ አመራሮች ፣ መምህራን  ፣ ተማሪዎችና መጋቢ እናቶች የትምህርት ቤት ምገባ ስርዓት መጠነ ማርፈድን ፣ መቅረትንና መድገምን በመቅረፍ የተማሪዎች ውጤት እንዲሻሸል ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ መሆኑ ገልጸዋል፡፡

የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር አቶ ቶፊቅ በድሩ በትምህርት ቤቱ የምገባ መርሀ ግብር በመኖሩ የተማሪዎች ውጤት እንዲሻሸል ፣ መጠነ መድገምና መቅረት እንዲቀንስ ትልቅ ሚና መጫወቱን  ገልጸው በ2016 ዓ.ም ትምህርት ቤቱ በ6ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ያሳለፋቸዉ ተማሪዎች 95 ፐርሰንት ከነበረበት በ2017 ዓ.ም 100 ፐርሰንት ተማሪዎችን ለማሳለፍ እዲሁም በ8ኛ ክፍል ከነበረበት 81 ፐርሰንት ወደ 98.3 ፐርሰንት ማሳደግ መቻሉን አመላክተዋል፡፡ በተጨማሪም 50 ፐርሰንት እና በላይ በማምጣት ከክፍል ክፍል የመዘዋወር ምጣኔ በ2016 ዓ.ም 95.4 የነበረ ሲሆን በ2017 ዓ.ም ወደ 98.4 ፐርሰንት ከፍ እንዲል ምገባው ከፍተኛ ሚና እያበረከተ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

የምገባ ስርዓቱ ለማህበረሰቡ ከፍተኛ እፎይታ የሰጠ ከመሆኑም ባሻገር የከተማ አስተዳደሩ የትምህርት ግብዓቶችን በማቅረቡ የመማር ማስተማር ስራዉ ስኬታማ እንዲሆን ላደረጉት ለክብርት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ፣ ለትምህርት ቢሮና ለምገባ ኤጀንሲ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

በትምህርት ቤቱ የሂሳብ መምህርት የሆኑት ሀይማኖት ነጋ በበኩላቸው ምገባው ከመጀመሩ በፊት ምግብ ሳይበሉ የሚመጡ ተማሪዎች በክፍል ውስጥ ያንቀላፉ እንደነበር እንዲሁም ለትምህርታቸው ትኩረት እንደማይሰጡ በዚህም በውጤታቸው ላይ ከፍተኛ ክፍተት ፈጥሮ እንደነበረ ገልጸው የምገባ ስርዓቱ ከተጀመረ በሓላ መጠነ መድገም ፣ ማቋረጥና መቅረት መቀረፉንና ተማሪዎች ለትምህርታቸው የሚሰጡት ትኩረት በማደጉ በተማሪዎች ውጤት ላይ ከፍተኛ መሻሻል እንዲመዘገብ ማስቻሉን አብራርተዋል፡፡

የዝግጅት ክፍላችን ያነጋገራቸው ተማሪዎችና መጋቢ እናቶችም በበኩላቸው በትምህርት ቤቱ እየተከናወነ የሚገኘው የምገባ ስርዓት የተማሪዎች ውጤት እንዲሻሻል ከማድረጉም ባለፈ ለበርካታ ወላጆችም የስራ እድል መፍጠሩን ጠቁመዋል፡፡ 

.

Copyright © All rights reserved.