የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት እና ወጣቶችና ስፖርት ቢሮዎች በሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ስፖንሰርነት በእቴጌ መነን የሴት ተማሪዎች አዳሪ ት/ቤት የሴቶች የ5 ኪሎሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ የማነቃቂያ የድላ ቅብብል ውድድር አካሂደዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ሲሳይ እንዳለ ቢሮ ትኩረት ሰጥቶ ከሚሰራባቸው አጀንዳዎች መካከል አንዱ ስፖርት መሆኑን ጠቅሰው በተማሪዎች መካከል የሚደረጉ ስፖርታዊ ውድድሮች በተማሪዎች መካከል ማህበራዊ መስተጋብሮች እንዲጎለብቱ ፤ በተሰማሩበት መስክ ላይ ውጤታማ እንዲሆኑ የሚረዳ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ አሰግዳው ሀይለጎርጊስ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ተማሪዎች ለትምህርታቸው የሚሰጡት ትኩረት እንዲዳብርና ለስነምግባር መዳበር ትልቅ ሚና እንዳለው ገልጸዋል፡፡
የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ተወካይ ያብስራ ጌታቸው የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ቅድሚያ ለሴቶች የ5 ኪሎሜትር የጎዳና ላይ ውድድር መጋቢት 13 ለ23ኛ ጊዜ የሚካሄድ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በመርሀ ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ አሰግዳው ሀይለጎርጊስ ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ሲሳይ እንዳለ ፣የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ ተስፋዮ አበራ ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ ዳዊት ትርፉ ፣ አትሌት መሰረት ደፋር ፣ ወ/ሮ ብርቱካን ሜደቅሳ ፣ የትምህርት ቤቱ ርዕሳነ መምህራን ፣ መምህራንና ተማሪዎች ተገኝተዋል፡፡
በተካሄደው የዱላ ቅብብል ውድድር አሸናፊ ለሆኑ ተማሪዎች መጋቢት 13 በሚካሄደው የ5 ኪሎሜትር የጎዳና ላይ ውድድር ለመሳተፍ የሚያስችል ቲሸርት ተበርክቶላቸዋል፡፡
.