የሚዲያ ይዘት ማበልፀግና ስርጭት ዳይሬክቶሬት በ3ኛ ሩብ ዓመት የትምህርት በሬዲዮ አተገባበር ላይ ለሚያደርገው ድጋፍና ክትትል ባዘጋጀው ቼክሊስት ላይ ማብራሪያ ሰጥቷል፡፡
የሚዲያ ይዘት ማበልፀግና ስርጭት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ የውብዳር አያሌው ለድጋፍና ክትትል በተዘጋጀ ቼክሊስት ላይ ገለጻ በተደረገበት ወቅት ላይ በቢሮው FM 94.7 ትምህርት በሬዲዮ ማስተላለፊያ ጣቢያ እየተሰጠ ያለው የሬዲዮ ትምህርት ትግበራ የትምህርት ተደራሽነትና ጥራትን ከማረጋገጥ ባለፈ ለማህበረሰቡ እያበረከተ ያለው ሚና ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል::
አያይዘውም ትምህርት በሬዲዮ አተገባበር በየጊዜው እየተሻሻለ መምጣቱን ገልጸው በ3ኛ ሩብ አመት የሚደረገው ድጋፍና ክትትል የትምህርት ስርዓቱን ለመደገፍና ወቅቱንና ጥራቱን የጠበቀ መረጃ ለማህበረሰቡ ተደራሽ ለማድረግ ቢሮው በልዩ ትኩረት እየሰራ መሆኑን እንደሚያሳይ ተናግረዋል፡፡ በድጋፍና ክትትሉ የሚሳተፉ ባለሙያዎችም የጠራ መረጃ በመያዝ ቀጣይ ለሚሰሩ ስራዎች ግብአት የሚሆኑና ክፍተቶችን ለመሸፈን የሚያስችል መረጃ ለማግኘት ድጋፍና ክትትሉን በትኩረት እንዲሰሩ አሳስበዋል፡፡
የስራክፍሉ አፋን ኦሮሞ ትምህርት ስርጭት ጣቢያ ሃላፊ አቶ ሴኔሳ ነጋሹ ለድጋፍና ክትትል የተዘጋጀ ቼክክሊስት ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
.