About በከተማ አስተዳደሩ በበይነ መረብ (online) ለሚሰጠው የ2017ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ የቅድመ ዝግጅት አካል የሆነ የሙከራ ፈተና በሁሉም የመፈተኛ ጣቢያዎች ተሰጠ።

በከተማ አስተዳደሩ በበይነ መረብ (online) ለሚሰጠው የ2017ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ የቅድመ ዝግጅት አካል የሆነ የሙከራ ፈተና በሁሉም የመፈተኛ ጣቢያዎች ተሰጠ።

25th June, 2025

በዛሬው እለት በተሰጠው የሙከራ ፈተና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ እና የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ አመራሮችን ጨምሮ በየደረጃው የሚገኙ የሁለቱ ሴክተር ባለሙያዎች በየፈተና ጣቢያው በመገኘት ሂደቱን የተከታተሉ ሲሆን በዛሬው እለት የተሰጠው የሙከራ ፈተና በስኬት መጠናቀቁን ከየፈተና ጣቢያው የተገኙ መረጃዎች ያሳያሉ።

የዛሬው የሙከራ ፈተና ከሰኔ 23/2017 ዓ.ም ጀምሮ ለሚሰጠው መደበኛ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በአግባቡ መዘጋጀት እንዲችሉ ምቹ ሁኔታ እንደፈጠረላቸው የሙከራ ፈተናውን የወሰዱ ተማሪዎች አረጋግጠዋል።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን ሙሉ ለሙሉ በበይነ መረብ ለመስጠት የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተከናወኑ የሚገኝ ሲሆን የዛሬው የሙከራ ፈተና ፈተናውን በበይነ መረብ ለመስጠት የተዘጋጁ የመሰረተ ልማቶች ብቁ መሆናቸውን ለማረጋገጥ የሚያስችል መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የትምህርት ቴክኖሎጂ እና መሰረተ ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ደረጀ ዳኜ አስታውቀዋል።

.

Copyright © All rights reserved.