About በትምህርት ሴክተሩ በርካታ ውጤታማ ተግባራት መከናወናቸውን በመስክ ምልከታ ማረጋገጡን ከከተማ አስተዳደሩ የተውጣጣ የሱፐርቪዥን ቡድን አስታወቀ።

በትምህርት ሴክተሩ በርካታ ውጤታማ ተግባራት መከናወናቸውን በመስክ ምልከታ ማረጋገጡን ከከተማ አስተዳደሩ የተውጣጣ የሱፐርቪዥን ቡድን አስታወቀ።

05th July, 2025

የሱፐርቪዥን ቡድን ከቢሮ ጀምሮ እስከ ትምህርት ቤት ድረስ ባካሄደው የድጋፍና ክትትል ግብረ መልስ ዙሪያ የቢሮው ስትራቴጂክ ካውንስል አባላት በተገኙበት ውይይት ተካሂዷል።

የሱፐርቪዥን ቡድኑ ከቢሮ ጀምሮ በተመረጡ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ባካሄደው የመስክ ምልከታ በርካታ ውጤታማ ስራ በመሰራት ላይ እንደሚገኝ መረጋገጡን በግብረ መልሱ የተገለጸ ሲሆን በ2017 ዓ.ም የተማሪዎችን የሒሳብና እንግሊዘኛ ውጤት ለማሻሻል የተዘጋጀው ስትራቴጂ በተማሪ ውጤት ላይ መታየት መጀመሩ ፣ በትምህርት ተቋማት መካከል ተቀራራቢ አፈጻጸም እንዲኖር ተከታታይ የድጋፍና ክትትል ስራ መሰራቱ ፣ የትምህርት ተደራሽነትን ለማረጋገጥ በርካታ ትምህርት ቤቶች መገንባታቸው ፣ የትምህርት ለትውልድ ንቅናቄን ውጤታማ ለማድረግ የ90 ቀን እቅድ ተዘጋጅቶ ወደ ተግባር መገባቱ ፣ የ2018 ዓ.ም እቅድ ከባለድርሻ አካላት ጋር የጋራ መደረጉ ፣ ከቢሮ ጀምሮ በየደረጃው የተቀናጀ አመራር በመፍጠር የመማር ማስተማር ሂደቱ የሚደገፍበት ስርአት መፈጠሩ እንዲሁም የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ የተሰሩ ስራዎች ሴክተሩ ውጤታማ እንዲሆን ከተከናወኑ ተግባራት መካከል የሚጠቀሱ መሆናቸው ተጠቁሟል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ የሱፐርቪዥን ቡድኑ ከቢሮ ጀምሮ እስከ ትምህርት ቤት ድረስ በመውረድ የትምህርት ዘርፉን ለመደገፍ ላደረገው ድጋፍና ክትትል ምስጋና አቅርበው በቀጣይ በሱፐር ቪዥን ቡድኑ የተሰጡ ግብረ መል ሶችን መሰረት በማድረግ የተሻለ ስራ እንደሚሰራ አስታውቀዋል።

.

Copyright © All rights reserved.