Announcement ሀገር አቀፍ የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

ሀገር አቀፍ የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

23rd August, 2025

በምክክር መድረኩ ላይ የ2017 ዓ.ም እቅድ አፈጻጸም በመገምገምና በ2018 ዓ.ም እቅድ ላይ በመምከር የሀገራችንን የትምህርት ስራዎች በላቀ ትጋት ለማስቀጠል በጋራ መስራት በሚገቡን ጉዳዮች ላይ ከመግባባት ላይ የምንደርሰበት ይሆናል።

በሀዋሳ ከተማ በመካሄድ ላይ በሚገኘው በዚህ በመርሃ ግብሩ ላይ የትምህርት ሚንስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ፣ የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ ፣ የሲዳማ ብ/ክ/መንግስት ም/ርዕሰ መስተዳድርና የትምህርት ቢሮ ሀላፊ አቶ በየነ በራሶ ፣ የከተማ አስተዳደርና የክልል ትምህርት ቢሮ ሀላፊዎችና ምክትል ቢሮ ሀላፊዎች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ፡፡

በምክክር መድረኩ ትምህርትን ለዜጎች በፍትሃዊነት ለማዳረስ የሚደረገውን ጥረት አጠናክሮ በማስቀጠል ረገድ ያሉ ጅምር ስራዎችን ማጠናከር እንደሚገባ ፣ በትምህርት ለትውልድ ንቅናቄ የተጀመሩ ስራዎች መጎልበት እንዳለባቸው ፣ የአምስት አመት የልማት መርሃ ግብር እንዲሁም የስድስተኛው የትምህርት ልማት መርሃ ግብር የሚጠናቀቅበት ወቅት በመሆኑ በ2018 ዓ.ም እቅድን ስኬታማ ለማድረግ በትኩረት መስራት እንዳለበት እንዲሁም የተገኙ ስኬቶችን ይበልጥ ለማዳበር ፣ ያጋጠሙ ችግሮችና ተግዳሮቶችን በልምድ ልውውጥና በሌሎች ስልቶችን በመንደፍ ለመፍታት እንዲያግዝ ታስቦ የተዘጋጀ ነው።

.

Copyright © All rights reserved.