Announcement የተማሪዎች የማለዳ የአካል ብቃት እንቅስቀሴ ማስጀመሪያ ከተማ አቀፍ መርሀ ግብር በዳግማዊ ሚኒሊክ ቅድመ አንደኛ አንደኛና መካከለኛ ደረጀ ትምህርት ቤት ተካሄደ፡፡

የተማሪዎች የማለዳ የአካል ብቃት እንቅስቀሴ ማስጀመሪያ ከተማ አቀፍ መርሀ ግብር በዳግማዊ ሚኒሊክ ቅድመ አንደኛ አንደኛና መካከለኛ ደረጀ ትምህርት ቤት ተካሄደ፡፡

11th October, 2025

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአራዳ ክፍለከተማ በሚገኘው ዳግማዊ ሚኒሊክ ቅድመ አንደኛ አንደኛና መካከለኛ ደረጀ  ትምህርት ቤት የተማሪዎች የማለዳ የአካል ብቃት እንቅስቀሴ ማስጀመሪያ መርሀ ግብር  "ብቁ እና ንቁ ትውልድ ለመፍጠር እንተጋለን!" በሚል መሪ ሀሳብ ተካሄዳል፡፡  

የአካል ብቃት እንቅስቃሴውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት እና ወጣቶችና ስፓርት ቢሮዎች በጋራ ያዘጋጁት ሲሆን በመድረኩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ  ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ ዲናኦል ጫላ ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ ዳዊት ትርፉ ፣ የክፍለ ከተማዉ ትምህርትና ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ሀላፊዎች ፣ የወረዳ ባለሙያዎችና አመራሮች ፣ የትምህርት ቤቱ መምህራን፣ አመራሮችና ተማሪዎች ተሳተፊ ሆነዋል፡፡ 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ ዲናኦል ጫላ ባስተላለፉት መልዕክት ተማሪዎች በአካልና በአዕምሮ ብቁ እንዲሆኑ ለማድረግ ስፖርታዊ እንቅስቀሴዎች ትልቅ አበርክቶ እንዳላቸው ገልጸው ስፖርት ግንኙነትን ለማጠናከርና ለአብሮነት የሚኖረው ሚና ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የስፓርት እንቅስቃሴው በየሳምንቱ 2 ጊዜ ጠዋት ጠዋት ማክሰኞና ሐሙስ በሁሉም በትምህርት ቤቶች በቋሚነት የሚካሄድ መሆኑን ገልፀዋል። ሀላፊው አክለውም የስፓርት ማስጀመሪያ ንቅናቄው በዛሬው እለት በሁሉም ክፍለ ከተማዎች የሚካሄድ መሆኑን ገልፀዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ ዳዊት ትርፉ በበኩላቸው በትምህርት ውጤት ላይ ብቻ ሳይሆን በአካል ብቁና ንቁ የሆኑ ተማሪዎችን በማፍራት ስራ ውስጥ የስፖርት መምህራን ትልቅ ሀላፊነት እንዳለባቸው እንዲሁም ንቅናቄው አመቱን ሙሉ በሁሉም ትምህርት ቤቶች ለ15 ደቂቃ የሚከናወን መሆኑን ገልፀዋል። በትምህርትና በወጣቶችና ስፖርት ቢሮዎች መካከለል በጋራ የሚከናወኑ ስራዎች ተጠናክረው የሚቀጥሉ እንደሚሆኑ ተናግረዋል፡፡

.

Copyright © All rights reserved.