ንቅናቄው "ብቁና ንቁ ትውልድ ለማፍራት እንተጋለን!" በሚል መሪ ቃል የተከናወነ ሲሆን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ለተማሪዎች የአዕምሮ እድገት አስተዋፅኦው የጎላ በመሆኑ ያንን ታሳቢ ያደረገ የማስ ስፖርት መርሀ-ግብር እንደሆነ በመድረኩ ላይ ተገልፁዋል፡፡
በመርሀ ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ አማካሪ አቶ ጥላሁን ፍቃዱና የክፍለ ከተማው ትምህርት ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ሰማኸኝ አስታጥቄ በዋሊያ ቅድመ አንደኛ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመገኘት አስጀምረዋል፡፡
በመድረኩ ከከተማ እስከ ወረዳ ያሉ አመራሮች የትምህርት ባለሙያዎች፣ሱፐርቫይዘሮች፣ የትምህርት ቤቱ መምህራን፣ የአስተዳደር ሠራተኞችና ተማሪዎች ተሳትፈዋል።
ይህ የማስ ስፖርት በሁሉም ትምህርት ቤቶች ዘወትር ማክሰኞ እና ሐሙስ ማለዳ የሚካሄድ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
.