About በኤች አይ ቪ ኤድስ ሜንስትሪሚንግ ላይ ትኩረት ያደረገ ስልጠና ተሰጠ::

በኤች አይ ቪ ኤድስ ሜንስትሪሚንግ ላይ ትኩረት ያደረገ ስልጠና ተሰጠ::

28th June, 2025

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ዘርፈ ብዙና ቀዳማይ ልጅነት ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት በኤች አይ ቪ ኤድስ ሜንስትሪሚንግ ላይ ትኩረት ያደረገ ስልጠና ሰጥቷል::

ኤች አይ ቪ ኤድስ ዛሬም ትውልድን እያጠቃ ያለ መድሀኒት ያልተገኘለት በሽታ መሆኑን ልብ ልንል ይገባል ያሉት የዘርፈ ብዙና ቀዳማይ ልጅነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ በላይነሽ የሻው በመክፈቻ ንግግራቸው ዜጎች ሁሉ በተለይም ትውልድ በመቅረፅ ላይ ያሉ የትምህርት ሴክተሩ አካላት የኤች አይቪ ኤድስን አስከፊነት በመረዳት ተማሪዎች ራሳቸውን ቤተሰቦቻቸውን እና ማህበረሰቡን መጠበቅ የሚያስችሉ ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎች ላይ እንዲሳተፉ ማድረግ ተገቢ መሆኑን ጠቁመዋል :: ዳይሬክተሯ አያይዘውም ኤች አይቪ  ለሕይወታችን ስጋት መሆኑ እስኪቀር ድረስ ግንዛቤ መፍጠራችንን አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል ::

.

Copyright © All rights reserved.