Announcement በጉለሌ ክፍለ ከተማ በአዲስ ዘመን ትምህርት ቤት ሳምንታዊ የፅዳት ዘመቻ ተካሄደ።

በጉለሌ ክፍለ ከተማ በአዲስ ዘመን ትምህርት ቤት ሳምንታዊ የፅዳት ዘመቻ ተካሄደ።

08th November, 2025

የጉለሌ ክፍለ ከተማ ፅዳትና ውበት አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መሰለ ይትባረክ በአዲስ ዘመን ት/ቤት በግንዛቤ ማስጨበጫው ላይ በመገኝት መልክት ያስተላለፉ ሲሆን በየእለቱ ፅዳትን የሚያዳብርና ፅዱና ውብ እንዲሁም ለነዋሪዎቹ ተስማሚ የሆነ ካባቢን በዘላቂነት ለመፍጠር ለታዳጊ ህፃናትና ለተማሪዎች ጠለቀ ያለ ግንዛቤ በመፍጠር የመማሪያ ስፍራዎችን ማፅዳትና ማስዋብ አስፈላጊ እንደሆነ ገልፀዋል።

የጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 አስተዳደር ዋና ስራ አስፍጻሚ አንዱዓለም አሸናፊ ፅዳትን ባህል ያደረገ ማህበረሰብ በመፍጠር ያማረ ውብና ፅዱ ት/ቤት እንዲሆን ለህብረተሰቡ እና ለተማሪዎች ግንዛቤ የመፍጠር ተግባር እንደተከናወነና ፅዳትን ባህል ያደረገ ተማሪን በማነፅ ትምህርት ቤቶችን ምቹ የመማሪያ ስፍራ በማድረግ በፅዳት ዘርፍ ለተማሪዎችን ምሳሌ በመሆን ያማረና ፅዱ ትምህርት ቤት መፍጠር የሁሉም ሰው ኃላፊነት እንደሆነ ገለፁ።

የጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ ዐ6 አስተዳደር የፅዳት እና ውበት አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አንዱዓለም አማረ እንደገለፁት ለተማሪዎችም ሆነ ለህብረተሰቡ ጠለቅ ያለ ግንዛቤ መስጠት ተገቢ እንደሆና ፅዳት እና ውበት አስተዳደር ፅህፈት ቤት ከትምህርት ጽ/ቤት ጋር በመቀናጀት በትምህርት ቤቶች ቅጥር ጊቢና አካባቢውን በማስዋብና በማፅዳት ምቹ የመማሪ ስፍራ እንደሚፈጥሩ ገልፀዋል።

.

Copyright © All rights reserved.