Home የከተማ አስተዳደሩ ትውልድ የመገንባት ስራ ከቀዳማይ ልጅነት ልማት (Early Childhood Development - ECD) እስከ ሕፃናት ማቆያ።

የከተማ አስተዳደሩ ትውልድ የመገንባት ስራ ከቀዳማይ ልጅነት ልማት (Early Childhood Development - ECD) እስከ ሕፃናት ማቆያ።

22nd November, 2025

ትምህርት ቤቶች የእውቀት ማዕከል እና ትውልድ የሚገነባባቸው ምሰሶዎች ናቸው።የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርም ይህንን በመረዳት  በተለይም በሕፃናት ማቆያና በቀዳማይ ልጅነት ልማት (Early Childhood Development - ECD) ላይ ሰፊ እና ውጤታማ ስራዎችን በመስራት ላይ ይገኛል።ከተማ አስተዳደሩ "ሕፃናት የአዲስ አበባ የኋለኛይቱ ተስፋ" በሚል መሪ ሃሳብ ስር አጠቃላይ እና ሁሉን አቀፍ የልማት ፕሮግራሞችን ቀይሶ በመተግበር የመዲናዋን የወደፊት ዕጣ ፈንታ ለመቀየር ትልቅ እርምጃ እየወሰደ ነው።

ከተማ አስተዳደሩ በሰራቸው ስራዎችም በአጭር ጊዜ ውስጥ ህፃናትን መሰረት ያደረጉ እውቅናዎችን ከአህጉራችን እንዲሁም ከአለም ማግኘት ችሏል።

በከተማ አስተዳደሩ  እየተሰሩ ከሚገኙ ስራዎች በጥቂቱ፦

1. የቀዳማይ ልጅነት (ECD) ሁለንተናዊ ልማት ስራዎች
የቀዳማይ ልጅነት ልማት (ከእርግዝና እስከ 6 ዓመት) በከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ ትኩረት የተሰጠው ሲሆን  ዓላማውም ዕድሜያቸው ከ6 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናት ጤናቸውን ፣ ትምህርታቸውን እና ሥነ-ልቦናዊ ደኅንነታቸውን ያካተተ ሁለንተናዊ እድገት እንዲያገኙ ማድረግ ነው።

2. በሕፃናት ማቆያ (Day Care Centers) የተሰሩ ቁልፍ ስራዎች

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሕፃናት ማቆያ ማዕከላትን ማስፋፋትና ማደራጀትን እንደ ዋነኛ ትኩረት ወስዷል። ይህ የሚደረገው ሴት ሰራተኞች ያለስጋት ስራቸውን እንዲሰሩ ምቹ ሁኔታን ከመፍጠር ባሻገር፣ ህፃናት እድሜያቸው ለትምህርት እስኪደርስ ድረስ ተገቢውን እንክብካቤና ማበረታቻ እንዲያገኙ ነው።

3. ዓለም አቀፍ እውቅና እና የልህቀት ማዕከል (Center of Excellence)

አዲስ አበባ ይህንን ሰፊ ስራ እየሰራች መሆኑ ዓለም አቀፍ ትኩረትን ስቧል።
👉 ዓለም አቀፍ የገንዘብ ድጋፍ እና አጋርነት

👉 አፍሪካ ለቀዳማይ ልጅነት ልማት ማዕከል (AfC-ECD)

እነኚህ አዲስ አበባ አለም አቀፍ እና አህጉር አቀፍ ትኩረትን የሳበችበት ሁነቶች ናቸው። አሁንም የከተማ አስተዳደሩ ከዚህ የላቀ ውጤት ለማስመዝገብ በስፋት እየሰራ ይገኛል።

.

Copyright © All rights reserved.