Announcement የተማሪዎች ውጤትና ስነምግባር በላቀ ሁኔታ እንዲሻሻል ወላጆች ኃላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ተገለፀ፡፡

የተማሪዎች ውጤትና ስነምግባር በላቀ ሁኔታ እንዲሻሻል ወላጆች ኃላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ተገለፀ፡፡

13th March, 2026

የተማሪዎች ውጤትና ስነምግባር በላቀ ሁኔታ እንዲሻሻል ወላጆች ኃላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባ የልደታ ክ/ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት በተማሪዎች ውጤት እና ስነምግባር ማሻሻል ዙሪያ ከተማሪ ወላጆች ጋር ባደረገው ውይይት ላይ የተገለጸ ሲሆን በመድረኩ የልደታ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ በላይነሽ ሞሲሳ ፣ የኢትዮጵያና የአዲስ አበባ  የተ.ወ.ማ ፕሬዝዳንት አቶ ሃሰን ሺፋ እና የትምህርት ጽ/ቤት የስራ አስተባባሪ አቶ አቡበከር አህመድ ፣ የክ/ከተማ ፣ የወረዳ እና የት/ቤት የተ.ወ.ማ አባላት ተገኝተዋል።

የልደታ ክ/ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ በላይነሽ ሞሲሳ የተማሪዎች ውጤት እና ስነምግባር በላቀ ሁኔታ እንዲሻሻል ወላጆች ኃላፊነታቸው መወጣት እንዳለባቸው ገልጸው ተማሪዎች ተገቢነትና ጥራት ያለው የትምህርት አገልግሎት እንዲያገኙ፣ ት/ቤቶች በግብዓት እንዲሟሉ እንዲሁም በት/ቤቶች ሠላማዊ የመማር ማስተማር ስራ በአግባቡ እንዲካሄድ ወላጆች እና የተማሪ ወላጅ ማህበር [ተ.ወ.ማ] የበኩላቸውን አስተዋፅኦ ማበርከት ይኖርባቸዋል ብለዋል።

የኢትዮጵያና የአዲስ አበባ የተ.ወ.ማ ፕሬዚዳንት አቶ ሃሰን ሺፋ በበኩላቸው ወላጆች ት/ቤቶችን በባለቤትነት፣ በተጠያቂነትና በተቆርቋሪነት መምራት እንደሚጠበቅባቸው ገልጸው በየት/ቤቱ ያሉ የተ.ወ.ማ አባላት በት/ቤት ግቢ ውስጥ በመገኘት አርፋጅ ተማሪዎችን የመምከር ፣ በሰልፍ ስነስርዓት የማስተባበር፣ የተማሪዎች ምገባን የማስተባበር እንዲሁም በጸጥታ ኮሚቴ ውስጥ በቀጥታ በመሳተፍ በት/ቤቶች ሠላማዊ የመማር ማስተማር ስራ እንዲካሄድ የማድረግ ኃላፊነትን መወጣት ያስፈልጋል ብለዋል።

የትምህርት ጽ/ቤት የስራ አስተባባሪ አቶ አቡበከር አህመድ የተማሪዎች ውጤት እና ስነምግባር በላቀ ሁኔታ እንዲሻሻል የተማሪ ወላጅ ማህበር ሚናን አቅርበው ውይይት ተካሂዳል፡፡

.

Copyright © All rights reserved.