የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የሚዲያ ይዘት ማበልፀግና ስርጭት ዳይሬክቶሬት እና የልዩ ፍላጎት አካቶ ትምህርት ትግበራ ዝግጅትና የጎልማሶች መሰረታዊ ትምህርት ትግበራ ዳይሬክቶሬት የ2017 በጀት ዓመት የግንቦት ወር 2 ሳምንታት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ለቢሮው ጠቅላላ ካውንስል አቅርበው ግምገማ ተካሂዷል::
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሲሳይ እንዳለ የስራ አፈፃፀም ሪፖርቶችን በየጊዜው መገምገም በጥንካሬ የሰራነውን ለማስቀጠልና እጥረቶች ላይ በአፋጣኝ እርማት ለመውሰድ እንደሚያስችል ገልፀዋል :: አያይዘውም በዚህ መድረክ የሚቀርቡ ሪፖርቶች የሪፎርም ሥራዎች ላይ የበለጠ ትኩረት ሰጥተው እንዲቀርቡ አሳስበዋል ::
የቢሮ ኃላፊ አማካሪ ወ/ሮ አበበች ነጋሽ በበኩላቸው የቀረቡ ሪፖርቶች ሥራዎቻችን በተቀመጠላቸው ወቅት በጥራት ለማጠናቀቅ የተሄደበትን ርቀት የሚያሳይ መሆኑን ተናግረዋል :: ሪፖርቶች ሲቀርቡ የሪፖርት መላኪያ ቢጋሩን በተከተለ መልኩ እንዲሆን እና የአቻ ፎረም መወያያ አጀንዳዎች ላይ ትኩረት በማድረግ ሊሆን ይገባል ብለዋል::
በዳይሬክቶሬቶቹ የሚሰጡ ዋናዋና አገልግሎቶች ውስጥ በ2ሳምንት የተከናወኑ አበይት ተግባራት ሪፖርት የሚዲያ ይዘት ማበልፀግና ስርጭት ዳይሬክተር ወ /ሮ የውብዳር አያሌው እና የልዩ ፍላጎት አካቶ ትምህርት ትግበራ ዝግጅትና የጎልማሶች መሰረታዊ ትምህርት ትግበራ ዳይሬክተር አቶ ገመቺስ ፈቃዱ አቅርበው ውይይት ተደርጎበታል ::
.