Home የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል እና የጸረ ሙስና እንቅስቃሴዉ ዉጤታማ ይሆን ዘንድ ላበረከተው አስተዋጽዖ እውቅና ተሰጠው፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል እና የጸረ ሙስና እንቅስቃሴዉ ዉጤታማ ይሆን ዘንድ ላበረከተው አስተዋጽዖ እውቅና ተሰጠው፡፡

13th December, 2025

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ብልሹ አሰራሮችን በመከላከል እና የጸረ ሙስና እንቅስቃሴዉ ዉጤታማ ይሆን ዘንድ ላበረከተው አስተዋጽዖ እውቅና ተሰጠው፡፡

(ታህሳሳ 3/2018 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ እውቅናዉን ያገኘው የአዲስ አበባ ከተማ ስነምግባር እና ጸረ ሙስና ኮሚሽን 22ኛውን የጸረ ሙስና ቀን ባከበረበት መድረክ ላይ ሲሆን እውቅናዉን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ አሊ ከማል ከአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አፈጉባኤ ወይዘሮ ቡዜና አልከድር እጅ ተቀብለዋል።

ከተማ አስተዳደሩ ሙስናን የሚጸየፍ ትውልድ ለመገንባት እያደረገ ያለው ጥረት ውጤታማ እንዲሆን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ከፍተኛ አበርክቶ እንዳለው ተገልጻል።

የአዲስ አበባ ከተማ ስነምግባር እና ጸረ ሙስና ኮሚሽን ያዘጋጀዉ 22ኛው ዓለም አቀፍ የጸረሙስና ቀን በስኬት እንዲጠናቀቅም ዉጤታማ አስተዋፅኦ ማድረጉ ተመላክቷል።


.

Copyright © All rights reserved.