የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የትምህርት ልማት ስራዉን ስኬታማነት ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ሁለገብ ተግባራትን በተለያዩ አግባቦች በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡
የከተማ አስተዳደሩ በ2018 የትምህርት ዘመን በልዩ ትኩረት እየሰራባቸው ከሚገኙ ተግባራት መካከል አንድ ደረጃቸዉን የጠበቁ የትምህርት ተቋማት ግንባታዎች ሲሆኑ የእነዚህ ግንባታዎች በፍጥነት መጠናቀቅና ለመማር መስተማር ስራው መዋል የክፍል ተማሪ ጥምርታን በስታንዳርድ ደረጃ እንዲሆን እንዲሁም የትምህርት ተደራሽነትን በማሻሻል የትምህርት ጥራት እንዲጎለብት ትልቅ ሚና ይጫወታል፡፡
በዕውቀትና በመልካም ሥነ-ምግባር የታነፀ ሀገር ተረካቢ ትውልድ ግንባታ ስራዉም ከዳር እንዲደርስ ትልቅ ድርሻም አለው፡፡ቢሮ በ2018 የትምህርት ዘመን 17 አዳዲስ ማለትም 7 ቅድመ አንደኛ ፣ 6 አንደኛና መካከለኛ ፣ 4 ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ፤ 27 ትምህርት ቤቶች ላይ የመጸዳጃ ቤቶችን ፤ በ2 አዳሪ ትምህርት ቤቶች ላይ 2 የG+4 መማሪያ ክፍሎች፣ ሁለገብ ህንጻዎችና የተማሪ ማሪፊያዎችን ግንባታዎች በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡
በክፍለ ከተማ በጀት G+0 መማሪያ ክፍል ብዛት 2 ፣ G+1 መማሪያ ክፍል ብዛት 1 ፣ G+2 መማሪያ ክፍል ብዛት 17 ፣ G+3 መማሪያ ክፍል ብዛት 1 ፣ G+4 መማሪያ ክፍል ብዛት 24 ፣ የተማሪዎች መጸዳጃ ቤቶች ብዛት 7 ፣ የስፖርት ሜዳዎች ብዛት 9 ፣ መመገቢያ አዳራሾች ብዛት ፣ ማብሰያ ክፍል ፣ የአጥር ገንባታዎች ብዛት 10 ፣ የምድረ ግቢ ግንባታዎች ብዛት 5 ፣ የጥበቃ ማማዎች ብዛት 2 በጥቅሉ 79 ደረጃቸዉን የጠበቁ ግንባታዎች በመከናወን ላይ ይገኛሉ፡፡
የመማሪያ ክፍሎች ግንባታ በፍጥነትና በጥራት እየተከናወኑ የሚገኙ መሆኑ የዝግጅት ክፍላችን ተዘዋውሮ በተመለከታቸው ክፍለ ከተማዎች ላይ ለማየት የቻለ ሲሆን የከተማ አስተዳደሩ በትምህርት ዘርፉ ላይ የሚያደርገው ይህ ኢንቨስትመንት ለመማር ማስተማር ሂደት ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር እና የትምህርት ጥራትን በዘላቂነት ለማረጋገጥ ድርሻው ትልቅ ነው።
.