Announcement የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽህፈት ቤት የሒሳብና እንግሊዘኛ ትምህርትን ተግባራዊ ለማድረግ በተዘጋጀው ስትራቴጂ ዙሪያ የአሰልጣኞች ስልጠና ሰጠ።

የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽህፈት ቤት የሒሳብና እንግሊዘኛ ትምህርትን ተግባራዊ ለማድረግ በተዘጋጀው ስትራቴጂ ዙሪያ የአሰልጣኞች ስልጠና ሰጠ።

15th November, 2025

የአሰልጣኞች ስልጠናው በክፍለ ከተማው በሚገኙ 1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሒሳብና እንግሊዘኛ ዲፓርትመንት ተጠሪ ለሆኑ መምህራን ፣ለሱፐርቫይዘሮች እንዲሁም ለወረዳ የስርአተ ትምህርት ቡድን መሪዎችና ክላስተር አስተባባሪዎች ነው የተሰጠው።

የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽህፈት ቤት የስራ አስተባባሪ እና የጽህፈት ቤት ኃላፊ ተወካይ አቶ ስለሺ ሶሪ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በ2017ዓ.ም የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ውጤትን መሰረት በማድረግ የተማሪዎችን የሒሳብና እንግሊዘኛ ትምህርት ውጤት ለማሻሻል ስትራቴጂ አዘጋጅቶ ተግባራዊ ማድረግ መጀመሩን ጠቁመው የዛሬው የአሰልጣኞች ስልጠና በክፍለ ከተማው በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ስትራቴጂው በአግባቡ ተግባራዊ እንዲሆን ግንዛቤ ለመፍጠር የሚያስችል መሆኑን አስታውቀዋል።

አቶ ስለሺ አያይዘውም የአሰልጣኞች ስልጠናው በዋናነት የሒሳብና እንግሊዘኛ ትምህርት የማስተማርያ ስነዘዴን መሰረት አድርጎ እንደመሰጠቱ የስልጠናው ተሳታፊዎች በየትምህርት ቤቱ ለሚገኙ መምህራን ተመሳሳይ ግንዛቤ መፍጠር እንደሚገባቸው ጠቁመው ክፍለ ከተማው በቀጣይ በየትምህርት ቤቱ በሚያደርገው ድጋፍና ክትትል አተገባበሩ ምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ የሚያረጋግጥ መሆኑን አስገንዝበዋል።

ስልጠናው ከብሪቲሽ ኢንተርናሽናል በመጡትና በዘርፉ ከፍተኛ የማሰልጠን ልምድ ባላቸው አቶ ቴውድሮስ አማካይነት ነው የተሰጠው።

.

Copyright © All rights reserved.