Announcement በአጭር ጊዜ ደረጃውን ጠብቆ የተገነባውና ለአገልግሎት የበቃው የቦሬ ገላን ቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት

በአጭር ጊዜ ደረጃውን ጠብቆ የተገነባውና ለአገልግሎት የበቃው የቦሬ ገላን ቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት

18th April, 2026

ከለውጡ ወዲህ የትምህርት ተደራሽነትንና ጥራትን ለማረጋገጥ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በትምህርት ዘርፍ ከተከናወኑ ግዙፍ ስራዎች አንዱ ደረጃቸዉን የጠበቁ የትምህርት ተቋማት ግንባታ ሲሆን ከነዚህ ትምህርት ተቋማት መካከል በንፈስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የሚገኘው የቦሬ ገላን ቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተጠቃሽ ነው፡፡ 

ይህ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ምቹ በሆነ አካባቢ እውቀትን እንዲቀስሙ ከማድረጉም ባለፈ የረጅም ጊዜ የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በአቅራቢያችን ይገንባልን የሚለዉን የአካባቢው ማህበረሰብን ጥያቄ ለመመለስ አስችላል፡፡ 

ይህ ተቋም የእውቀት ማዕከል ብቻ ሳይሆን እያንዳንዱ ህፃን ትምህርት የማግኘት ሰብአዊ መብቱን በተግባር ለመረጋገጡ ማሳያ ጭምር ነው።

ይህም የትምህርት መሰረተ ልማቶች ግንባታ በፍጥነት በጥራትና በአስደናቂ ሁኔታ እየተገነቡ ለመማር ማስተማር ስራዉ እየዋሉ መሆናቸዉን ከማሳየቱም ባሻገር ትምህርትን እድሜው ለትምህርት ለደረሰ ለሁሉም ዜጋ ተደራሽ ለማድረግ በተያዘው ግብ ውስጥ ትልቅ ድርሻ ያለው ነው።

.

Copyright © All rights reserved.