Home መምህራንና ተማሪዎች ከትምህርት ሰዓት ውጪ የአቅመ ደካማ አርሶ አደሮችን የመኸር የእርሻ ምርት ሰብል አጨዳ እና መሰብሰብ መርሃ-ግብር ላይ ተሳተፉ።

መምህራንና ተማሪዎች ከትምህርት ሰዓት ውጪ የአቅመ ደካማ አርሶ አደሮችን የመኸር የእርሻ ምርት ሰብል አጨዳ እና መሰብሰብ መርሃ-ግብር ላይ ተሳተፉ።

06th December, 2025

አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የአርሶ አደርና የከተማ ግብርና ጽ/ቤት ከክፍለ ከተማው የህብረተሰብ ተሳትፎ እና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ጋር በመተባበር በወረዳ 09 አስተዳደር የአቅመ ደካማ አርሶ አደር የደረሰ የመኸር እርሻ ምርት ሰብል አጨዳ እና መሰብሰብ መርሃ-ግብር ተካሄዳል።

በመርሃ ግብሩ የክፍለ ከተማው ዋና አፈ-ጉባኤ የተከበሩ አቶ ሙሉጌታ አሰፋን ጨምሮ ፣ የክፍለ ከተማና የወረዳ አመራሮች ፣ በጎ ፈቃደኞች ፣ መምህራንና ተማሪዎች ፣ የደንብ ማስከበር ኦፊሰሮች ፣ የፀጥታ አካላት እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል ።

የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ዋና አፈ-ጉባኤ የተከበሩ አቶ ሙሉጌታ አሰፋ በመርሃ-ግብሩ ባስተላለፉት መልዕክት አቅመ ደካማ አርሶ አደርን ማገዝ የህሊና ዕረፍትን የሚሰጥ መሆኑን በማንሳት በክፍለ ከተማው  በርካታ የግብርና ስራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኝና ይህም ከተሜነት ከግብርናው ተነጥሎ ሊሰፋ የማይችል መሆኑን ማሳያ እንደሆነ ገልፀው ሁሉም ባለድርሻ አካላት አቅመ ደካማ አርሶ አደሮችን በቻለው ሁሉ ሊደግፍ እንደሚገባ ተናግረዋል ።


.

Copyright © All rights reserved.