የካራአሎ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች በክፍል ውስጥ የተማሩት የኢትዮጵያ ህዝቦች የሉዓላዊነት፣ የአንድነትና የነጻነት ታላቅ ተጋድሎ የሆነውን የዓድዋ ድል ታሪክ በዓድዋ ድል መታሰቢያ በመገኘት ትምህርታዊ ጉብኝት አድርገዋል፡፡
ከካራአሎ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ10ኛ ክፍል ተማሪዎች ስለ ዓድዋ ጦርነት ከየት ጀምሮ፤ የት እና እንዴት ተጠናቀቀ የሚለውን ከመጀመሪያው እስከመጨረሻው የነበረውን ታሪክ በትምህርታዊ ጉብኝቱ በአካል ተገኝተው በመመልከታቸው እንደተደሰቱ ገልፀዋል።
በትምህርታዊ ጉብኝቱ ላይ የተገኙ መምህራን በበኩላቸው የዓድዋ ድል መታሰቢያ የእውቀት ማዕከል ከመሆን ባሻገር ተማሪዎች ባዩት ነገር ስለአንድነት እንዲማሩ እድል የሰጠ እንዲሁም በቀጣይ ለሃገራችን ምን ሰርተን እንለፍ የሚለውን ሃሳብም በአዕምሮአቸው እንዲያሰላስሉ እና በተሰማሩበት ዘርፍ ሁሉ ብቁ ዜጋ እንዲሆኑ የሚያደርግ ነው ብለዋል፡፡
.