የከተማ አስተዳደሩ ባለፉት የለውጥ አመታት ለትምህርት ዘርፉ ልዩ ትኩረት በመስጠት ባደረገው ከፍተኛ ኢንቨስትመንት መሰረት አበረታች ውጤቶች የተመዘገቡ ሲሆን በበጀት ዓመቱ በ 6 ወራት በተሰራዉ ስራ
ከተማሪዎች ውጤት አንጻር፤ የ6ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና 50% በላይ ያመጡ ተማሪዎች 2015 ዓ.ም ከነበረበት 80.2% በአሁን ወቅት 95% ማድረስ ተችሏል::
የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና 50% በላይ ያመጡ ተማሪዎች 2010 ዓ.ም ከነበረበት 36.1% በአሁን ወቅት ወደ 88.8% ከፍ ብሏል።
12ኛ ክፍል ሃገር አቀፍ ፈተና 50% በላይ ያመጡ ተማሪዎች 2013 ዓ.ም ከነበረበት 25.45% በአሁን ወቅት 31% ከፍ ማለቱ እና በመንግስትና በግል ትምህርት ቤቶች መካከል የነበረውን የውጤት ልዩነት በከፍተኛ ደረጃ ተቀራራቢ የአፈጻጸም ውጤት እንዲመዘገብ አስችሏል፡፡
የትምህርት ተሣትፎና ፍትሐዊነት በማሳደግ በዕውቀትና በሥነ- ምግባር የታነፀ ትውልድን ለማፍራት ከቅድመ አንደኛ ደረጃ እስከ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት አጠቃላይ ተማሪ ቅበላ ከነበረበት 1,253,737 ወደ 1,334,830 የደረሰ ሲሆን ካለፈው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የተማሪ ቁጥር 81,093 ዕድገት አሳይቷል።
የትምህርት ፍትሃዊነትና አካታችነትን ለማስፈን በተደረገው ጥረት በሁሉም ት/ቤቶች የልዩ ፍላጎት ትምህርትን በማስፋፋት በጥቅሉ 124 ማእከላትን ማድረስ ተችሏል፡፡
በ80 ት/ቤቶች ራምፕ ጥገና እና ራምፕ በሌላቸው 4 ት/ቤቶች በአዲስ መልክ የመገንባት ሥራ ፤ ለአይነ ስውራን ተማሪዎች የብሬል መፅሃፍ ህትመት በማከናወን ስራ እንዲሁም ለ36 ትምህርት ቤቶች ለተማሪዎች እና ለመምህራኑ ስፈላጊ ሆኑ ግበዓቶች እንዲሟሉ ተደርጓል::
የት/ቤቶችን መሠረተ ልማት ለማሻሻል ባለፉት 6 ወራት “ትምህርት ለትውልድ” ንቅናቄ በተሰራው ሥራ ተለያዩ ባለድርሻ አጋር አካላትን በትምህርት ጥራት ላይ ተሳትፎአቸዉን በማጠናከር በጥሬ ገንዘብ 637,253,857፤ በዓይነት 1,137, 493,918፤ በጉልበት 211,388,874፣በዕቀውት 243,478,637 በድምሩ 1.32 ቢሊየን ለመሰብሰብ ታቅዶ ክንውን 2.23 ቢሊየን (100% በላይ) ሀብት ማሰባሰብ ተችሏል፡፡
በተማሪዎች ምገባ፤- በቅድመ አንደኛ እና አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ላይ 940,329 በላይ ተማሪዎች በቀን ሁለት ጊዜ እንዲመገቡ እየተደረገ ሲሆን የተማሪ ዩኒፎርም፣ የትምህርት ቁሳቁስ እና የመምህራን ጋዋን በወቅቱ እንዲደርሳቸው በማድረግ በኢኮኖሚያዊ ጫና ምክንያት ትምህርታቸውን የሚያቋርጡ ተማሪዎች (መጠነ ማቋረጥ)፤የሚደግሙ (ተማሪዎች መጠነ መድገም) ጉልህ በሆነ መልኩ መቀነስ እንዲሁም በተማሪዎች መካከል የእኩልነት ስሜት በማዳበር የስነ ልቦና ጫናን መቀነስ ተችሏል፡፡
ከንቲባ አዳነች አቤቤ