Announcement የመምህራንን መረጃ ወደ ኢ-ስኩል ሲስተም በማስገባት የመማር ማስተማር ስራውን ውጤታማ ማድረግ እንደሚገባ ተገለጸ።

የመምህራንን መረጃ ወደ ኢ-ስኩል ሲስተም በማስገባት የመማር ማስተማር ስራውን ውጤታማ ማድረግ እንደሚገባ ተገለጸ።

16th August, 2025

 የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የመምህራን እና የትምህርት አመራር ልማት ዳይሬክቶሬት ከቢሮው የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ልማትና ማስፋት ዳይሬክቶሬት ጋር በመሆን የመምህራንን አጠቃላይ መረጃ ወደ ኢ-ስኩል ሲስተም በማስገባት የመማር ማስተማር ስራው ውጤታማ እንዲሆን የሚያስችል ስልጠና ለክፍለ ከተማ የመምህራን ልማት ቡድን መሪዎች እና ባለሙያዎች እንዲሁም ለአይ ሲቲ እና መረጃ ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች ሰቷል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የመምህራ እና የትምህርት አመራር ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ አበራ ስልጠናው በዋናነት በኢ-ስኩል ሲስተም አማካይነት የመምህራንን ቅጥር፣ዝውውር እና ሌሎች መረጃዎችን በመሙላት የመማር ማስተማር ስራውን ውጤታማ ለማድረግ እንዲቻል ታስቦ መዘጋጀቱን ጠቁመው ቢሮው በቅርቡ የሰራው የመምህራን የውስጥ ዝውውር እና ሽግሽግን ሲስተሙን መሰረት አድርጎ  መረጃ የመምህራኑ ወደ ተመደቡበት ክፍለ ከተማ መላኩን በመግለጽ  መረጃው ወደ ኢ-ስኩል ሲስተም ያልገባ መምህር ዝውውርን ጨምሮ ሌሎች አገልግሎቶችን ማግኘት ስለማይችል በቀጣይ ርዕሳነ መምህራንን ጨምሮ ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት የመምህራኑን መረጃ ወደ ሲስተም ማስገባት እንደሚኖርባቸው አስገንዝበዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ልማትና ማስፋት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ደረጀ ዳኜ በበኩላቸው ሁለቱ ዳይሬክቶሬቶች በጋራ ከሚያከናውኗቸው ተግባራት መካከል  የመምህራን ቅጥርን እና ዝውውርን ጨምሮ አጠቃላይ መረጃዎችን ወደ ኢ-ስኩል ሲስተም ማስገባት አንዱ መሆኑን ገልጸው  የመምህራኑ መረጃ ወደ ሲስተም መግባቱ የሚያስተምሩት የትምህርት አይነት እና የተመደቡበትን ሴክሽን በሲስተሙ አማካይነት በቀላሉ ለማወቅ እንደሚያግዝ አስረድተዋል።

መረጃው ወደ ኢ-ስኩል ሲስተም ያልገባ መምህር በ2018 ዓ.ም የትምህርት አመት ሴክሽን የማይመደብ ከመሆኑ ባሻገር የተማሪ አቴንዳንስና ውጤት መሙላት ስለማይችል   የመምህራኑን መረጃ ከወዲሁ ወደ ሲስተም ማስገባት እንዲቻል ስልጠናው ሲስተሙን ባለማው ትሪያ ትሬዲንግ አማካይነት መሰጠቱን የቢሮው ሲስተም አስተዳደር ቡድን መሪ ወይዘሮ ሰላማዊት ተስፋዬ ገልጸዋል።


.

Copyright © All rights reserved.