ዛሬ የገላን ጉራ የመኖሪያ እና የተቀናጀ የልማት መንደርን መርቀን ከካዛንቺስ በልማት ለተነሱ ነዋሪዎቻችን አስረክበናል።
(ህዳር 30/2017 ዓ.ም) የኢትዮጵያ መልክ የሆነችው አዲስ አበባን እንደ ስሟ ውብ አበባ ለማድረግ በገባነው ቃል መሰረት፣ መሰረተ ልማት ከማሟላት በተጨማሪ የሰው አኗኗርን ማሻሻል እና የነዋሪዎቻችንን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ትልቅ ትኩረት ሰጥተን በመስራት ላይ እንገኛለን።
ነዋሪዎቻችንን ካረጀ እና ለመኖር ምቹ ካልሆነ የካዛንቺስ አካባቢ እንዲወጡ አድርገን ለኑሮ ምቹ የሆነ ቤት እና አካባቢ እንዲገቡ ያደረግን ሲሆን በዚህም የሰው ህይወትን የመቀየር ስራን ሰርተናል።
ከካዛንቺስ አካባቢ ለልማት በፈቃደኝነት የተነሳችሁ እና ከጎናችን የቆማችሁ ነዋሪዎችን ስለ ትዕግስታችሁ እና ድጋፋችሁ እያመሰገንኩ፣ ይህ ስራ እንዲሳካ ህግ እና አሰራሩን በመቀበል ቦታውን በፈቃደኝነት ለልማት የለቀቃችሁ የአካባቢው አርሶ አደሮችንም ላመሰግናቸው እወዳለሁ።
ይህን ታላቅ ስራ በአጭር ጊዜ ውስጥ ገንብታችሁ ያጠናቀቃችሁ ኮንትራክተሮችን፣ አማካሪ ድርጅቶችን፣ ድጋፍ ያደረጋችሁ አካላትን፣ ያስተባበራችሁ አመራሮችን እንዲሁም የክፍለከተማው አመራሮችን በራሴ እና በከተማ አስተዳደራችን ስም ላመሰግናችሁ እወዳለሁ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ