About በትምህርት ቤቶች አካባቢ የመማር ማስተማሩን ሂደት በሚያውኩ ተግባራት በተሰማሩ ተቋማት ላይ እርምጃ እየወሰድን ነው፡- የአዲስ አበባ ፖሊስ

በትምህርት ቤቶች አካባቢ የመማር ማስተማሩን ሂደት በሚያውኩ ተግባራት በተሰማሩ ተቋማት ላይ እርምጃ እየወሰድን ነው፡- የአዲስ አበባ ፖሊስ

24th May, 2025

በትምህርት ቤቶች አካባቢ የመማር ማስተማሩን ሂደት በሚያውኩ ተግባራት በተሰማሩ ተቋማት ላይ እርምጃ እየወሰድን ነው፡- የአዲስ አበባ ፖሊስ

(ግንቦት 15/2017 ዓ.ም) በአዲስ አበባ ከተማ በተከናወነው ተከታታይ የግንዛቤ ማስጨበጥ ሥራ ከባድ ወንጀሎች ቀንሰዋል ሲሉ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የሕዝብ ግኑኝነት ዳይሬክተር ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ ተናግረዋል።  

ኮማንደር ማርቆስ በኤፍኤም አዲስ 97.1 አሼ ታለንት የመዝናኛ እና የመረጃ ፕሮግራም ላይ እንደተናገሩት፥ በሕብረተሰቡ ዘንድ በተሰራው ተከታታይነት ያለው የግንዛቤ ማስጨበጥ ሥራ በከተማዋ የሚፈጸሙ ወንጀሎች በ43 በመቶ ቀንሰዋል።  

በከተማዋ በተከናወኑ የአደባባይ በዓላት እና የጎዳና ላይ ዝግጅቶች የወጣቶች ሚና የጎላ እንደነበር ኮማንደር ማርቆስ ገልጸው፤ የከተማዋ ወጣቶች ወንጀሎችን በመከላከል ከጸጥታ አካላት ጋር ለሚያደርጉት ትብብር ፖሊስ ምስጋና ያቀርባል ብለዋል።

ባለፉት 9 ወራት የሚፈጸሙ ወንጀሎችን ለመቀነስ በተሰሩ ሥራዎች፣ በሁሉም ክፍለ ከተሞች የወንጀሎች መነሻ ናቸው ተብለው በተለዩ 6 ሺህ 128 የሺሻ እና የጫት ቤቶች ላይ እርምጃ ተወስዷል ሲሉ ተናግረዋል። ይህም ወንጀል እንዲቀንስ አንዱ ምክንያት መሆኑን ነው የተናገሩት።

በትምህርት ቤቶች አካባቢ የመማር ማስተማሩን ሂደት በሚያውኩ ተግባራት በተሰማሩ ተቋማት ላይ እርምጃ እየወሰድን ነው ያሉት ኮማንደር ማርቆስ ፤ በዚህ ሕግ የማስከበር  ሥራ ሕብረተሰቡ ከጎናችን ሊሆን ይገባል ሲሉ ጥሪ ማቅረባቸዉን ኢቢሲ ዘግባል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! 

https://linktr.ee/aacaebc

.

Copyright © All rights reserved.