(ሚያዝያ 3 /2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የልዩ ፍላጎት /አካቶ ትምህርትና ጎልማሶች መሰረታዊ ትምህርት ትግበራ ዳይሬክቶሬት የስራ ክፍሉ ባለሙያዎች እና በሁሉም ክፍለ ከተሞች የሚገኙ የክፍለ ከተማ የዘርፉ ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች በተገኙበት የ 9ወራት የሥራ አፈፃፀሙን ገምግማል።
የልዩ ፍላጎት/አካቶ ትምህርትና ጎልማሶች መሰረታዊ ትምህርት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ገመቺስ ፍቃዱ በ9 ወራት የተከናወኑ ዋና ዋና ሥራዎችን አቅርበው ውይይት የተደረገበት ሲሆን በተቀመጠው እቅድ መሰረት ከልዩ ፍላጎትና ጎልማሶች ትምህርት ጋር የተያያዘ በርካታ ተግባራቶች መከናወናቸውን ገልፀዋል::
አቶ ገመቺስ በቀጣይ እንደ ሥራ ክፍል በበጀት ዓመቱ ለመስራት የተቀመጡና በ9ወራት ያልተከናወኑ ቀሪ ሥራዎችን በመለየት ትኩረት ተደርጎ የሚሰራ መሆኑን ተናግረዋል::