Announcement ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ለሚማሩ አይነስውር ተማሪዎች የተዘጋጀ የብሬል መጽሐፍ ግምገማ በመካሄድ ላይ መሆኑ ተገለጸ።

ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ለሚማሩ አይነስውር ተማሪዎች የተዘጋጀ የብሬል መጽሐፍ ግምገማ በመካሄድ ላይ መሆኑ ተገለጸ።

23rd August, 2025

የብሬል መጽሐፍ ግምገማው በከተማ አስተዳደሩ ከሚገኙ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በተውጣጡ አይነስውር መምህራን እና በቢሮ የሁለቱ ስርአተ ትምህርት ባለሙያዎች አማካይነት በመካሄድ ላይ መሆኑን ከልዩፍላጎትና ጎልማሶች መሰረታዊ ትምህርት ዳይሬክቶሬት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የልዩፍላጎትና ጎልማሶች መሰረታዊ ትምህርት ዳይሬክቶሬት ተወካይ አቶ ጌታቸው በላይነህ ከተማ አስተዳደሩ የልዩፍላጎት ተማሪዎችን በትምህርት ስርአቱ ተጠቃሚ ለማድረግ  ተጨባጭ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ መሆኑን ጠቁመው ትምህርታቸውን ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል በመከታተል ላይ ለሚገኙ አይነስውራን ተማሪዎች ተዘጋጅቶ በመገምገም ላይ የሚገኘው የብሬል መጽሐፍ የዚሁ ተግባር ማሳያ መሆኑን አመላክተዋል።

አቶ ጌታቸው አያይዘውም የብሬል መጽሐፍ ግምገማው ዛሬን ጨምሮ ለተከታታይ አራት ቀናት እንደሚካሄድ ጠቁመው ግምገማው ከተጠናቀቀ በኋላ የሚሰጡ የማስተካከያ ሀሳቦች ተካተው ለህትመት የሚላክ መሆኑን አስገንዝበዋል።

የቢሮው የልዩፍላጎትና አካቶ ትምህርት ባለሙያ አቶ ጸጋዬ ሁንዴ በበኩላቸው የብሬል መጽሐፎቹ በ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሚማሩ አይነስውር ተማሪዎችን ተጠቃሚ ለማድረግ ዳይሬክቶሬቱ ከቢሮው ስርአተ ትምህርት ባለሙያዎች እና የብሬል ክህሎት ካላቸው አይነስውር መምህራን ጋር በጋራ ማዘጋጀቱን ገልጸው ግምገማው ሲጠናቀቅ መጽሐፍቶቹን በማሳተም በ2018 ዓ.ም የትምህርት አመት ለተማሪዎች ተደራሽ እንደሚደረጉ አስታውቀዋል።

.

Copyright © All rights reserved.