Welcome to AACEB
+913222224
|
info.aaceb@addislearning.edu.et
|
Help center
Home
Calender
Authentication & Equivalency
Survey
About
Resource
Back
Resource
Educational Statics
Legal Document
Schools
More
Home
Login
About
ማርች 8 የሴቶች ቀን በእቴጌ መነን የሴቶች 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተከበረ::
ማርች 8 የሴቶች ቀን በእቴጌ መነን የሴቶች 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተከበረ::
22nd March, 2025
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በዓለም አቀፍ ለ114 ኛ በሀገራችን ለ 49ኛ ጊዜ የሚከበረው ማርች 8 የሴቶች ቀን በእቴጌ መነን ልጃገረዶች 2 ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አክብሯል ::
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ወንድሙ ዑመር በአሉ ሲከበር ተገኝተው ባስተላለፉት መልእክት በየዓመቱ የሚከበረው የሴቶች ቀን ሴቶች አይችሉም የሚል ጫናን በመጣል በማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ተሳትፎ ከወንዶች እኩል መቻላቸውን ለማሳየት የተከፈለ ትግል ውጤት የምናስብበት ነው በማለት አብራርተዋል ::
ሴቶች ምቹ ሁኔታና ዕድል ካገኙ የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ እንደሚችሉ የተናገሩት ምክትል ቢሮ ኃላፊው የመነን ልጃገረዶች ትምህርት ቤት ተማሪዎች ለዚህ ማሳያ ይሆናሉ ብለዋል:: አክለውም በአሉን በዚህ ትምህርት ቤት ስናከብር ቤተሰብና ሃገር ከናንተ ብዙ ውጤት እንደሚጠብቅ የቤት ሥራ ለመስጠት ነው ብለዋል ::
የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህርት ወ/ሮ ሃና ፀጋዬ በበኩላቸው ለእቴጌ መነን የልጃገረዶች 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ሁልጊዜ የሴቶች ቀን ነው በማለት ተማሪዎቹን ያበረታቱ ሲሆን ሴቶች መቻላችሁን በተግባር ለማሳየት ውጤታማነት ላይ በትኩረት እንድትሰሩ በማለት አሳስበዋል::
በመርሃ ግብሩ ላይ በትምህርት ቤቱ ከ7ኛ እስከ 12ኛ ክፍል በአጠቃላይ ውጤት ከፍተኛ ነጥብ ላስመዘቡ ተማሪዎች ሽልማት ተበርክቶላቸዋል::
በተጨማሪም በአሉን የተመለከቱ ግጥሞች አጭር ድራማና ስነፅሁፋዊ ሥራዎች በተማሪዎች የቀረበ ሲሆን የምኒልክ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ማርች ባንድ አባላት በበአሉ ላይ በመገኘት ከበዓሉ ጋር የተገናኙ ጥዑመ ዜማዎችን አቅርበዋል ::
ማርች 8 የሴቶች ቀን በዘንድሮው ዓመት "ፈጣንና ቀጣይነት ያለው ሁሉን አቀፍ ለውጥ በሴቶች ተሳትፎ ይረጋገጣል!" በሚል መሪ ቃል በተለያዩ መርሀግብሮች እየተከበረ መቆየቱ ይታወሳል ::
.