በምልከታው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱን ጨምሮ የአራዳ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ወንድሙ ኡመር እና የክፍለ ከተማው ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ዱጋሳ ፍቃዱ ተገኝተዋል።
ብሔራዊ ቤተመንግስት አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ምድረ ግቢው ጠባብ ከመሆኑ የተነሳ የተማሪዎች መማሪያ ክፍል ጥበትና የአስተዳደር ስራዎችን ለመስራት የሚያስችል የቢሮ እጥረት በመኖሩ ከትምህርት ቤቱ ማህበረሰብና ከወላጆች የሚነሱ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመቅረፍ እንዲቻል በትምህርት ቤቱ ምልከታ መደረጉን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ አስታውቀዋል።
ኃላፊው አያይዘውም በቀጣይ የትምህርት ቤቱን ቅጥር ግቢ ለተማሪዎች ምቹ የመማሪያ ስፍራ እንዲሆን የማስዋብና የአስተዳደር ስራዎችን መስራት የሚያስችሉ ተጨማሪ ቢሮዎች ተገንብተው ከህብረተሰቡ የሚነሱ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ምላሽ እንዲያገኙ ለክፍለከተማው አስተዳደር አቅጣጫ መሰጠቱን አመላክተዋል።
.