Home በልደታ ክፍለከተማ 11ኛዉ ክፍለ ከተማ አቀፍ የተማሪዎች ሊግ እና የመምህራን ስፖርታዊ ዉድድር መርሃ-ግብር ተጠናቀቀ።

በልደታ ክፍለከተማ 11ኛዉ ክፍለ ከተማ አቀፍ የተማሪዎች ሊግ እና የመምህራን ስፖርታዊ ዉድድር መርሃ-ግብር ተጠናቀቀ።

24th January, 2026

በልደታ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት አስተባባሪነት ለቀናት ሲካሄድ የነበረዉን ስፖርታዊ ዉድድር መርሃ ግብር አሸናፊዎችን  መሸለም ተጠናቋል። 

በመዝጊያ ፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ አማካሪ አቶ ጥላሁን ፍቃዱ እንደገለፁት በአካላዊ ብቃት የዳበረ ትዉልድ  ጤነኛ፣ በአስተሳሰብ የበቃ ዜጋን ማፍራት ብሎም በሀገር ደረጃ ለተያዘዉ ስፖርታዊ የለዉጥ ነቅናቄ ምልመላ ትልቅ አስተዋጽኦ ያለዉ መሆኑን ገልፀዋል።

በልደታ ክፍለከተማ ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ኃላፊ የሆኑት  አቶ አሰፋ ቶላ እንዳሉት ይህ አይነቱ ዉድድር ለትዉልድ ግንባታ የሚኖረዉ ሚና ከፍተኛ ስለሆነ የበለጠ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል።

የልደታ ክፍለከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ በላይነሽ ሞሲሳ በመዝጊያ ዝግጅቱ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ለቀናት ሲካሄድ የነበረዉ ይህ ዉድድር አላማዉ በአካላዊ ብቃት የዳበረ፣ በትምህርት ዉጤት የበቃና ለሀገር ብልፅግና ጉልህ አስተዋፅኦ የሚወጣ ዜጋን ማፍራት ነዉ ሲሉ ገልፀዋል። 

11ኛዉ ዙር ክፍለ ከተማ አቀፍ የተማሪዎች ስፓርታዊ ሊግና የመምህራን ስፖርታዊ ዉድድር ለዉድድሩ አሸናፊዎች ከሜዳሊያ እስከ ዋንጫ በመሸለም ተጠናቋል።


.

Copyright © All rights reserved.