ለ2018 የትምህርት ዘመን ጥራቱን የጠበቀ የደንብ ልብስ ለተማሪዎች ለማቅረብ እንዲቻል ጥራቱን ለማረጋገጥ በከተማ ደረጃ ለተቋቋመው የጥራት ኮሚቴ ኦረንቴሽን ተሰጠ፡፡
(ግንቦት 28/2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተደደር ትምህርት ቢሮ ለ2018 የትምህርት ዘመን የተማሪዎች የደንብ ልብስ ለማቅረብ ጨረታ ያሸነፉ ድርጅቶች ወደ ምርት ከመግባታቸዉ በፊት ጥራቱን ለማረጋገጥ በከተማ ደረጃ ለተቋቋመው የጥራት ኮሚቴ ኦረንቴሽን ሰጥቷል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተደደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ ሳምሶን መለስ ለ2018 የትምህርት ዘመን ጥራቱን የጠበቀ የደንብ ልብስ ለተማሪዎች ለማቅረብ እንዲቻል በከተማ ደረጃ ጨረታ ወጥቶ አሸናፊዎች መለየታቸዉን በመግለጽ ያሸነፉ ድርጅቶች ወደ ምርት ከመግባታቸዉ በፊት ጥራቱን ለማረጋገጥ በከተማ ደረጃ ለተቋቋመው የጥራት ኮሚቴ ኦረንቴሽን መሰጠቱን ገልጸዋል፡፡
አቶ ሳምሶን አክለዉም ኮሚቴው ጨረታዉን ባሸነፉ በ21 ዱም ጋርመንቶች በመሄድ ክትትልና ቁጥጥር ማድረግ እንደሚገባውና በሚፈለገው ልክ ጥራቱ የተጠበቀ የተማሪዎች የደንብ ልብስ እንዲሰፋ ትልቅ ሀላፊነትና አደራ ጭምር የተጣለበት መሆኑን ተናግረዋል፡፡
.