የአዲስ አየአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ስትራቴጂክ ካውንስል አባላት የ2018 የትምህርት ዘመንን መሪ እቅድ ገመገሙ።
(ግንቦት 29/2017) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የስትራቴጂክ ካውንስል አባላት የቢሮውን የ2018 የትምህርት ዘመንን ረቂቅ መሪ እቅድ የገመገሙ ሲሆን እቅድ በቢሮ የእቅድ ዝግጅትና ክትትል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በሆኑት በአቶ ጌታሁን ለማ ቀርቧል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ በ2017 ትምህርት ዘመን የተመዘገቡትን አበረታች ውጤቶች እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀምና አጠናክሮ በማስቀጠል የታዩ ጉድለቶችን ለይቶ በማስተካከል በቀጣይ በ2018 ትምህርት ዘመን ውጤታማ ስራ ለመስራት የሚያስችሉ አራት ስትራቴጂክ ትኩረት መስኮች ላይ መሰረት በማድረግ ተቋማዊ የማስፈጸም አቅምን ፣ የሀብት አጠቃቀም እና የአገልግሎት አሰጣጥ አሰራር ማጎልበትን ፤ የአጠቃላይ ትምህርት ፍትሃዊ ተደራሽነትን ማረጋገጥን ፤ ጥራትና ተገቢነት ያለው መማር ማስተማር እና የትምህርት ውስጣዊ ብቃት ማሳደግ በሚሉት ላይ በትኩረት በመስራት የትምህርት ሴክተሩን አጠቃላይ ትምህርት ተልዕኮ፣ ራዕይና ፣ ዕሴቶችን ለማሳካት ይሰራል ብለዋል፡፡
ሀላፊው አክለዉም የጸደቀው የ2018 የትምህርት ዘመን ሪቂቅ መሪ እቅድ በቀጣይ ከትምህርት ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት የሚደረግበተና በሚሰጡ ግብዓቶች ተካተው የሚዳብር መሆኑን ገልጸዋል፡፡በባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ስትራቴጂክ ካውንስል አባላት የ2018 የትምህርት ዘመንን መሪ እቅድ ገመገሙ።
በቢሮ የእቅድ ዝግጅትና ክትትል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጌታሁን ለማ እቅድ ነባራዊ ሁኔታን ከሃገራዊ፣ ከተማ አቀፍና ተቋማዊ ሁኔታ ጋር በመዳሰስ ፤ ዋና ዋና የአፈጻጸም ስትራቴጅዎችና አቅጣጫዎችን በመለየት የ2018 ትምህርት ዘመን ግቦችና ፤ ዋና ዋና ተግባራትና የውጤት ዓመላካቾች ተለይተው በእቅዱ ውስጥ መካተታቸዉን ተናግረዋል፡፡
.