በአካሉ ብቁና በአዕምሮው ንቁ ትውልድ ለሀገር ብልጽግና"በሚል መሪ ቃል ሲካሄድ በቆየው ክፍለ ከተማ አቀፍ ውድድር በክፍለከተማው ከሚገኙ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ ተማሪዎች እና መምህራን በተለያዩ የስፖርት አይነቶች ተወዳድረው አሸናፊ ለሆኑት በክብር እንግዶች የዋንጫ እና ሜዳልያ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
የቦሌ ክፍለ ከተማ ውና ስራ አስፈጻሚ እና የመዝጊያ መርሀግብሩ የክብር እንግዳ ዶክተር እሸቱ ለማ በትምህርት ቤቶች የሚካሄድ ስፖርታዊ ውድድር ተማሪዎች በአካል ብቃታቸው ዳብረው በትምህርታቸው ውጤታማ እንዲሆኑ ከማስቻሉ ባሻገር በተወዳዳሪ ተማሪዎችና መምህራን መካከል ወዳጅነትን የሚያጠናክር መርሀግብር መሆኑን ገልጸው ውድድሩ በስኬት እንዲጠናቀቅ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት ምስጋና በማቅረብ የክፍለ ከተማው አስተዳደር በቀጣይ ክፍለ ከተማውን ወክለው በከተማ ደረጃ በሚካሄደው ውድድር ለሚሳተፉ ተወዳዳሪዎች የሚያስፈልገውን ድጋፍ የሚያደርግ መሆኑን አስገንዝበዋል።
የቦሌ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ መስፍን ታደሰ በበኩላቸው የተማሪዎች የስፖርት ሊግ እና የመምህራን ውድድር ሁለንተናዊ ስብዕናው የተገነባ ትውልድ ከመፍጠር ባሻገር ተተኪ ስፖርተኞችን ለማፍራት የሚያስችል መርሀግብር መሆኑን ጠቁመው በክፍለ ከተማ ደረጃ በተካሄደው ውድድር አሸናፊ በመሆን የተመረጡ ተወዳዳሪዎች በቀጣይ በከተማ ደረጃ በሚካሄድ ተመሳሳይ መርሀግብር ክፍለ ከተማውን ወክለው የሚሳተፉ መሆኑን አስገንዝበዋል።
ትምህርት ቤቶች የታዳጊ ስፖርተኞች መገኛ እንደመሆናቸው በክፍለ ከተማ ደረጃ የተካሄደው ውድድር ተተኪ ስፖርተኞች የተገኙበት መሆኑን የክፍለ ከተማው ወጣቶችና ስፖርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አንዱአለም አሰፋ ገልጸው ውድድሩ ስኬታማ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ጽህፈት ቤቱ ድጋፍ የሚያደርጉ ባለሙያዎችን እና ዳኞችን ከመመደብ ጀምሮ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት ሲሰራ መቆየቱን አስታውቀዋል።
በቦሌ ህብረተሰብ ትምህርት ቤት በነበረው የመዝጊያ መርሀ ግብር የቡልቡላ 2ኛ ደረጃ እና የቦሌ ህብረተሰብ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የፍጻሜ የእግር ኳስ ጫወታ አካሂደው ቦሌ ህብረተሰብ 4 ለ 1 በማሸነፍ የዋንጫ ተሸላሚ የሆነ ሲሆን በመርሀግብሩ በክፍለ ከተማው ከሚገኙ ወረዳዎች የተውጣጡ ተማሪዎችና መምህራን የተለያዩ ብሔረሰቦችን አልባሳት ተጠቅመው ትርኢቶችን ለታዳሚው አቅርበዋል።
.