Announcement የ2018 ትምህርት ዘመን ጥናትና ምርምር ስራ 1ኛ ሩብ ዓመት እቅድ አፈፃፀም ላይ ውይይት ተካሄደ::

የ2018 ትምህርት ዘመን ጥናትና ምርምር ስራ 1ኛ ሩብ ዓመት እቅድ አፈፃፀም ላይ ውይይት ተካሄደ::

18th October, 2025

አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ2018 ትምህርት ዘመን የጥናትና ምርምር ስራዎች 1ኛ ሩብ ዓመት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ውይይት ተካሄደ:: 

የመምህራንና ትምህርት አመራር ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ አበራ በውይይቱ መክፈቻ ባደረጉት ንግግር እንዳሉት ለትምህርት ሴክተሩ አስፈላጊ የሆኑና በተማሪ ውጤትና ስነምግባር ላይ ለውጥ የሚያመጡ ጥናትና ምርምር ስራዎች ለመስራት ከቢሮ ጀምሮ እስከ ክፍለ ከተማ ድረስ በትኩረት ሲሰራ መቆየቱን ተናግረው ጥናትና ምርምሩ የትምህርት ጥራትን ለማምጣትና በስነምግባር የታነፀ ትውልድ ለማፍራት ያለው አስተዋፅኦ ከፍተኛ ነው ብለዋል ::

አቶ ተስፋዬ አያይዘውም የዚህ የሩብ ዓመት የስራ ግምገማ ቀጣይ መምህራን ለሚሰሩት ተግባራዊ ጥናትና ምርምር ስራ ቅርብ የሆነ ድጋፍና ክትትል ለማድረግና በትስስር የሚሰሩ ሥራዎች የሚፈልጉትን አቅም በማወቅ ረገድ መነሻ የሚሆን ሀሳብ የሚገኝበትና በምን መልኩ መደገፍ እንዳለብን ግንዛቤ የምንወስድበት ይሆናል ብለዋል ::

በውይይቱ የክፍለ ከተማ ጥናትና ምርምር ባለሙያዎች እና የሶስቱ አዳሪ ትምህርት ቤቶች ጥናትና ምርምር ባለሙያዎች የተሳተፉ ሲሆን የጥናትና ምርምር ስራው 1ኛ ሩብ ዓመት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት በአቶ ዮሐንስ ተስፋዬ አማካኝነት ቀርቦ በተሳታፊዎች ውይይት ተደርጎበታል::

.

Copyright © All rights reserved.