(መስከረም 5/2018 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ከለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አድማሱ ደቻሳ ፣ከትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ወንድሙ ኡመር ፣ከምገባ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ፀዳለች ሚካሄል እንዲሁም ከትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ ወይዘሮ ሌሊስቱ ተስፋዬ ጋር በመሆን በዱዱቢሳ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተገኝተው የአዲሱን አመት ትምህርት በማስጀመር ተማሪዎችን አበረታተዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ በከተማ አስተዳደሩ በ2017 ዓ.ም በትምህርት ሴክተሩ ባለድርሻ አካላትን በማስተባበር በተከናወኑ ተግባራት በዘርፉ በርካታ ውጤት መመዝገቡን ጠቁመው በ2018ዓ.ም የትምህርት አመት አምና የተገኙ ውጤቶችን አጠናክሮ በማስቀጠል የተማሪዎች ውጤትና ስነምግባር እንዲሻሻል ሁሉም ባለድርሻ ኃላፊነቱን በአግባቡ እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።
የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አድማሱ ደቻሳ በበኩላቸው ዱዱቢሳ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በክፍለ ከተማው በርካታ ተማሪዎችን ተቀብለው ከሚያስተምሩ የትምህርት ተቋማት መካከል አንዱ እንደመሆኑ በ2018 ዓ.ም የትምህርት አመት በተቋሙ ተጨማሪ የመማሪያ ክፍሎችን የያዘ ህንጻን ጨምሮ የመመገቢያ አዳራሽ እና የስፖርት ማዘውተሪያ ሜዳ መገንባቱን ገልጸው የክፍለ ከተማው አስተዳደር ለትምህርት ቤቱ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን አመላክተዋል።
በትምህርት ቤቱ የ2018 ዓ.ም ትምህርት መጀመሩን የሚያበስር ችቦ ከመብራቱ ባሻገር የትምህርት መማሪያ ቁሳቁስ በክብር እንግዶች አማካይነት ለተማሪዎች ተሰቷል።
.