በመድረኩ የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ቡዜና አልከድር የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክታቸውን ካስተላለፉ በኋላ ይህ ግምገማ በበጀት ዓመቱ መጀመሪያ ላይ በተፈራረምነው የዋና ዋና ግቦች ዕቅድን መነሻ ያደረገ እንደሆነና ይህንንም መነሻ አድርጎ ቋሚ ኮሚቴው በየሩብ ዓመቱ እየገመገመ መምጣቱንና በዚህም የተሰሩ ስራዎች ምን ውጤት አስገኝተዋል የሚለውን አድምጦ በቀጣይ አጠቃላይ ሪፖርት እንደሚያቀርብ ክብርት አፈ ጉባኤ ገልፀዋል።
በዛሬው መድረክም የትምህርት ቢሮ ሪፓርት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ የቀረበ ሲሆን ማጠቃለያ ሪፖርቱን ምክር ቤቱ በማዳመጥ ገምግማል።
.