የአራዳ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት የ2017 ዓ.ም የክረምት የተማሪዎችና የመምህራን ስፖርት ንቅናቄ ማስጀመርያ መርሃ ግብር በዳግማዊ ሚኒሊክ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አካሂዷል።
በመርሃ ግብሩ ላይ በክፍለ ከተማው ስር የሚገኙ ከሁሉም ትምህርት ቤቶች የተወጣጡ መምህራን፣ የትምህርት ቤት አመራሮች፣ ተማሪዎች እና የትምህርት ባለሙያዎች የተሳተፉ ሲሆን በዕለቱም ሁሉም አካላትን ባሳተፈ መልኩ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ተደርጓል።
በንቅናቄ መስጀመሪያው ላይ የአራዳ ክፍለ ከተማ ትምህርት ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ደሣለኝ ደበሌ ትውልድን በአካል ብቃት እና በስነልቦና ማብቃት አንዱ የትምህርት ተግባር እንደሆነና በHንድሮም አመት በክረምት ወቅት በሁሉም ትምህርት ቤቶች የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ያለማቋረጥ መካሄድ ስላለበት ከዛሬ ጀምሮ ባሉት ቀናት ተማሪዎች እና መምህራን እንዲሁም የትምህርት ማህበረሰቡ የሚሣተፋበት የስፖርት እንቅስቃሴ እንደ አንድ ተግባር ተወስዶ በልዩ ትኩረት እንደሚሰራ አሳውቀዋል ።
.